በቀጥታ ወደ ዋናው ጉዳይ ግባ

በቀጥታ ወደ ርዕስ ማውጫው ሂድ

ክርስቲያናዊ ሕይወት

በመስከረም ወር የመጠበቂያ ግንብ መጽሔት ለማበርከት የሚደረግ ልዩ ዘመቻ

በመስከረም ወር የመጠበቂያ ግንብ መጽሔት ለማበርከት የሚደረግ ልዩ ዘመቻ

በዛሬው ጊዜ፣ እያንዳንዱ ሰው ማጽናኛ ማግኘት ያስፈልገዋል። (መክ 4:1) በመሆኑም በመስከረም ወር ስለ ማጽናኛ የሚናገረውን የመጠበቂያ ግንብ እትም ለማበርከት ልዩ ጥረት እናደርጋለን። ይህን መጽሔት በስፋት ለማሰራጨት የተቻለንን ሁሉ እናደርጋለን። ሆኖም ሰዎችን ለማጽናናት እነሱን በአካል ማነጋገር ስላለብን ቤት ላልተገኙ ሰዎች መጽሔቱን በራቸው ላይ ትተን አንሄድም።

ምን ማለት እንችላለን?

“ማናችንም ብንሆን በሆነ ወቅት ላይ ማጽናኛ ማግኘት ያስፈልገናል። ግን ማጽናኛ ማግኘት የምንችለው ከየት ነው? [2 ቆሮንቶስ 1:3, 4ን አንብብ።] ይህ የመጠበቂያ ግንብ እትም አምላክ ማጽናኛ የሚሰጠን እንዴት እንደሆነ ያብራራል።”

ግለሰቡ ፍላጎት ካለውና መጽሔቱን ከወሰደ ደግሞ . . .

መጽሐፍ ቅዱስን መማር የሚኖርብን ለምንድን ነው? የሚለውን ቪዲዮ አሳየው።

መጽሐፍ ቅዱስ እንዲያጠና ግብዣ አቅርብለት።

ለተመላልሶ መጠይቅ መሠረት ጣል

ተመልሰህ ስትመጣ ልትመልስለት የምትችል አንድ ጥያቄ አንሳ፤ ለምሳሌ “አምላክ መከራ እንዲኖር የፈቀደው ለምንድን ነው?” ብለህ ልትጠይቀው ትችላለህ።