በቀጥታ ወደ ዋናው ጉዳይ ግባ

በቀጥታ ወደ ርዕስ ማውጫው ሂድ

ክርስቲያናዊ ሕይወት

በአገልግሎት ረገድ ክህሎታችንን ማዳበር—JW.ORGን መጠቀም

በአገልግሎት ረገድ ክህሎታችንን ማዳበር—JW.ORGን መጠቀም

አስፈላጊ የሆነው ለምንድን ነው? ለማስተማር በምንጠቀምባቸው መሣሪያዎች ውስጥ የተካተቱት የሕትመት ውጤቶች በሙሉ ወደ jw.org ይመራሉ። እንዲያውም የአድራሻ ካርዳችን እንዲሁም በአእምሯችን ለሚጉላሉ ጥያቄዎች መልስ ማግኘት የሚቻለው ከየት ነው? የተባለው ትራክት ዋነኛ ዓላማ ሰዎችን ከድረ ገጻችን ጋር ማስተዋወቅ ነው። jw.orgን ተጠቅመን የኤሌክትሮኒክ ቅጂዎችን ኢ-ሜይል በማድረግ ወይም ጽሑፉ የሚገኝበትን አድራሻ (ሊንክ) በመላክ ለማስተማር በምንጠቀምባቸው መሣሪያዎች ውስጥ የተካተቱትን የሕትመት ውጤቶች ማበርከት እንችላለን። በተለይም ሌላ ቋንቋ ለሚናገር ሰው በምንመሠክርበት ጊዜ ይህን አማራጭ ጠቃሚ ሆኖ እናገኘዋለን። በተጨማሪም አገልግሎት ላይ የምናገኛቸው ሰዎች ከሚያነሷቸው ጥያቄዎች መካከል አንዳንዶቹ መልሳቸው ለማስተማር በምንጠቀምባቸው መሣሪያዎች ውስጥ አይገኝ ይሆናል። ድረ ገጹን በሚገባ የምንጠቀም ከሆነ በአገልግሎታችን ይበልጥ ውጤታማ መሆን እንችላለን።

ይህን ማድረግ የሚቻለው እንዴት ነው?

  • የመጽሐፍ ቅዱስ ትምህርቶች” የሚለውን ክፍል ተጠቀም። ለምሳሌ ያህል፣ ልጆችን ስለማሳደግ ይበልጥ ማወቅ ለሚፈልግ ወላጅ ስትመሠክር የመጽሐፍ ቅዱስ ትምህርቶች > ትዳር እና ቤተሰብ የሚለውን ክፍል መጠቀም ትችላለህ።

  • የሕትመት ውጤቶች” የሚለውን ክፍል ተጠቀም። ለምሳሌ ያህል፣ ትምህርት ቤት ውስጥ መደበኛ ባልሆነ መንገድ ስትመሠክር አብሮህ ለሚማር ተማሪ የወጣቶች ጥያቄ የተባለውን መጽሐፍ ማበርከት ፈለግክ እንበል። የሕትመት ውጤቶች > መጻሕፍትና ብሮሹሮች የሚለውን ክፍል ከፍተህ መጽሐፉን ማግኘት ትችላለህ።

  • ስለ እኛ” የሚለውን ክፍል ተጠቀም። ለምሳሌ ያህል፣ ለሥራ ባልደረባህ ስትመሠክርለት ስለምናምንባቸው ነገሮች አጠር ያለ ማብራሪያ ማግኘት እንደሚፈልግ ገለጸልህ እንበል። ስለ እኛ > ብዙ ጊዜ የሚነሱ ጥያቄዎች የሚለውን ክፍል ከፍተህ ልታሳየው ትችላለህ።

JW.ORGን መጠቀም የሚለውን ቪዲዮ ተመልከት፤ ከዚያም የሚከተሉትን ሰዎች ለመርዳት ድረ ገጻችን ላይ የሚገኘውን የትኛውን ክፍል እንደምትጠቀም ለማሰብ ሞክር፦

  • በአምላክ መኖር የማያምን ሰው

  • በቅርቡ አሳዛኝ ነገር ያጋጠመው ሰው

  • የቀዘቀዘ ወንድም ወይም የቀዘቀዘች እህት

  • የይሖዋ ምሥክሮች ለሥራቸው የሚያስፈልጋቸውን ገንዘብ የሚያገኙት እንዴት እንደሆነ ማወቅ የሚፈልግ ተመላልሶ መጠየቅ

  • በሚኖርበት አገር ስብሰባዎች ላይ መገኘት የሚፈልግ ከሌላ አገር የመጣ ሰው