ክርስቲያናዊ ሕይወት
ኢየሱስ ለወንድምህም ጭምር ሞቶለታል
ኢየሱስ ፍጹም ላልሆኑ ሰዎች ሕይወቱን መሥዋዕት አድርጓል። (ሮም 5:8) ኢየሱስ ሕይወቱን በመስጠት ለእኛ በግለሰብ ደረጃ ፍቅር እንዳሳየን ማስታወስ አይከብደን ይሆናል። ሆኖም ክርስቶስ ለእኛ ብቻ ሳይሆን ለወንድማችንም ጭምር እንደሞተለት መዘንጋት አይኖርብንም። ልክ እንደ እኛ ፍጹማን ላልሆኑ ወንድሞቻችንና እህቶቻችን የክርስቶስን ዓይነት ፍቅር ማሳየት የምንችለው እንዴት ነው? ሦስት መንገዶችን እንመልከት። አንደኛ፣ ከእኛ የተለየ አስተዳደግ ካላቸው ሰዎች ጋር ጭምር ለመቀራረብ ጥረት ማድረግ እንችላለን። (ሮም 15:7፤ 2ቆሮ 6:12, 13) ሁለተኛ፣ ሌሎችን ቅር ሊያሰኝ የሚችል ነገር ከመናገር ወይም ከማድረግ ለመቆጠብ ጥረት ማድረግ ያስፈልገናል። (ሮም 14:13-15) በመጨረሻም፣ የበደሉንን ሰዎች ይቅር ለማለት ፈጣኖች መሆን አለብን። (ሉቃስ 17:3, 4፤ 23:34) በእነዚህ መንገዶች ኢየሱስን ለመምሰል ብርቱ ጥረት የምናደርግ ከሆነ ይሖዋ ሰላምና አንድነት በመስጠት ጉባኤውን መባረኩን ይቀጥላል።
ይበልጥ ውብ መሆን! የሚለውን ቪዲዮ ተመልከት፤ ከዚያም የሚከተሉትን ጥያቄዎች ለመመለስ ሞክር፦