በቀጥታ ወደ ዋናው ጉዳይ ግባ

በቀጥታ ወደ ርዕስ ማውጫው ሂድ

ክርስቲያናዊ ሕይወት

የምታከናውኑት መልካም ሥራ አይረሳም

የምታከናውኑት መልካም ሥራ አይረሳም

የይሖዋ ሕዝቦች በሙሉ ለአምላካችን ቅዱስ አገልግሎት በማቅረብ የማይረሳ ታሪክ ማስመዝገብ ይችላሉ። አንድ አፍቃሪ ወላጅ ልጆቹ ያከናወኑትን መልካም ሥራ ምንጊዜም ከፍ አድርጎ እንደሚመለከት ሁሉ ይሖዋም የምናከናውነውን ሥራ እንዲሁም ለስሙ የምናሳየውን ፍቅር መቼም ቢሆን አይረሳም። (ማቴ 6:20፤ ዕብ 6:10) እርግጥ ነው፣ የእያንዳንዳችን ችሎታና ሁኔታ ይለያያል። ያም ቢሆን በይሖዋ አገልግሎት ምርጣችንን የምንሰጥ ከሆነ ደስታ እናገኛለን። (ገላ 6:4፤ ቆላ 3:23) ባለፉት ዓመታት በሺዎች የሚቆጠሩ ወንድሞችና እህቶች በቤቴል አገልግለዋል። በቤቴል ለማገልገል ራስህን በፈቃደኝነት ማቅረብ ትችላለህ? ካልሆነ በዚህ አገልግሎት እንዲካፈል ልታበረታታው የምትችለው ሰው አለ? ወይም የቤቴል ቤተሰብ አባል የሆነ ክርስቲያን በዚህ አገልግሎቱ እንዲቀጥል መርዳት ትችል ይሆን?

ለቤቴል አገልግሎት ራስህን ማቅረብ ትችል ይሆን? የሚለውን ቪዲዮ ተመልከት፤ ከዚያም የሚከተሉትን ጥያቄዎች ለመመለስ ሞክር፦

  • አንድ ክርስቲያን በቤቴል ለማገልገል ራሱን እንዲያቀርብ ሊያነሳሳው የሚገባው ምንድን ነው?

  • በቤቴል ማገልገል ስለሚያስገኛቸው በረከቶች አንዳንዶች ምን ብለዋል?

  • በቤቴል ለማገልገል የሚያስፈልጉት ብቃቶች ምንድን ናቸው?

  • በቤቴል ለማገልገል ማመልከት የምትችለው እንዴት ነው?