ክርስቲያናዊ ሕይወት
ጊዜህን ይሖዋን ከሚወዱ ሰዎች ጋር አሳልፍ
ጊዜያችንን ይሖዋን ከሚወዱ ሰዎች ጋር ማሳለፋችን አስፈላጊ የሆነው ለምንድን ነው? አብረናቸው የምንሆናቸው ሰዎች በጥሩም ሆነ በመጥፎ ተጽዕኖ ስለሚያደርጉብን ነው። (ምሳሌ 13:20) ንጉሥ ኢዮዓስን እንደ ምሳሌ እንውሰድ፤ ኢዮዓስ፣ ከሊቀ ካህኑ ከዮዳሄ ጋር በነበረበት ጊዜ ሁሉ “በይሖዋ ፊት መልካም የሆነውን ነገር [አድርጓል]።” (2ዜና 24:2) ዮዳሄ ከሞተ በኋላ ግን ኢዮዓስ መጥፎ ጓደኝነት ስለመሠረተ ይሖዋን ማገልገሉን ተወ።—2ዜና 24:17-19
በመጀመሪያው መቶ ዘመን፣ ሐዋርያው ጳውሎስ የክርስቲያን ጉባኤን ‘ከአንድ ትልቅ ቤት’ ጋር፣ የጉባኤውን አባላት ደግሞ በቤት ውስጥ ካሉ ‘ዕቃዎች’ ጋር አመሳስሏቸው ነበር። “ክብር ላለው ዓላማ የሚያገለግል . . . መሣሪያ” መሆን ከፈለግን ይሖዋን የሚያሳዝን ነገር ከሚያደርግ ማንኛውም ሰው ጋር አንቀራረብም፤ ይህ የቤተሰባችንን ወይም የጉባኤያችንን አባላትም ይጨምራል። (2ጢሞ 2:20, 21) ምንጊዜም ቢሆን ወዳጆቻችን ይሖዋን የሚወዱና እሱን እንድናገለግለው የሚያበረታቱን ሰዎች ሊሆኑ ይገባል።
ከመጥፎ ጓደኛ ራቁ የሚለውን ቪዲዮ ተመልከት፤ ከዚያም የሚከተሉትን ጥያቄዎች ለመመለስ ሞክር፦
-
መጥፎ ተጽዕኖ ከሚያሳድሩብን ሰዎች ጋር እንድንቀራረብ የሚያደርጉን አንዳንድ ሁኔታዎች የትኞቹ ናቸው?
-
በቪዲዮው ላይ የታዩት ሦስት ክርስቲያኖች መጥፎ ተጽዕኖ ከሚያሳድሩ ሰዎች ጋር ያላቸውን ቅርርብ ለማቋረጥ የረዳቸው ምንድን ነው?
-
ጓደኞችህን በጥበብ ለመምረጥ የሚረዱህ የመጽሐፍ ቅዱስ መሠረታዊ ሥርዓቶች የትኞቹ ናቸው?