የካቲት 1-7
ነህምያ 1–4
መዝሙር 126 እና ጸሎት
የመግቢያ ሐሳብ (3 ደቂቃ ወይም ከዚያ በታች)
ከአምላክ ቃል የሚገኝ ውድ ሀብት
“ነህምያ እውነተኛውን አምልኮ ይወድ ነበር”፦ (10 ደቂቃ)
[የነህምያ መጽሐፍ ማስተዋወቂያ የተባለውን ቪዲዮ አጫውት።]
ነህ 1:11–2:3—ነህምያ የእውነተኛው አምልኮ መስፋፋት የደስታ ምንጭ ሆኖለታል (w06 2/1 9 አን. 7)
ነህ 4:14—ነህምያ ይሖዋን ማሰቡ ከእውነተኛው አምልኮ ጋር በተያያዘ ያጋጠመውን ተቃውሞ እንዲያሸንፍ ረድቶታል (w06 2/1 10 አን. 2)
መንፈሳዊ ዕንቁዎችን በምርምር ማግኘት፦ (8 ደቂቃ)
ነህ 1:1፤ 2:1—በነህምያ 1:1 እና 2:1 ላይ የተጠቀሰው “20ኛው ዓመት” የተሰላው ከተመሳሳይ ጊዜ ተነስቶ ነው የምንለው ለምንድን ነው? (w06 2/1 8 አን. 5)
ነህ 4:17, 18—በመልሶ ግንባታው ላይ የተሠማራ ሰው በአንድ እጁ መሥራት የሚችለው እንዴት ነው? (w06 2/1 9 አን. 1)
የዚህ ሳምንት የመጽሐፍ ቅዱስ ንባብ ስለ ይሖዋ ምን ያስተምረኛል?
የዚህ ሳምንት የመጽሐፍ ቅዱስ ንባብ ለመስክ አገልግሎት ሊጠቅሙኝ የሚችሉ ምን ነጥቦች ይዟል?
የመጽሐፍ ቅዱስ ንባብ፦ ነህ 3:1-14 (4 ደቂቃ ወይም ከዚያ በታች)
በአገልግሎት ውጤታማ ለመሆን ተጣጣር
የዚህን ወር መግቢያዎች ተዘጋጅ፦ (15 ደቂቃ) በውይይት የሚቀርብ። እያንዳንዱን የአቀራረብ ናሙና ቪዲዮ አጫውት፤ ከዚያም ጎላ ባሉ ነጥቦች ላይ ተወያዩ። አስፋፊው ለተመላልሶ መጠየቅ እንዴት መሠረት እንደጣለ ጎላ አድርገህ ግለጽ። አስፋፊዎች የራሳቸውን መግቢያ እንዲያዘጋጁ አበረታታ።
ክርስቲያናዊ ሕይወት
መዝሙር 103
በመጋቢት ወይም በሚያዝያ ወራት ረዳት አቅኚ ሆናችሁ ለማገልገል ከአሁኑ ዕቅድ አውጡ፦ (15 ደቂቃ) በውይይት የሚቀርብ። “የመታሰቢያው በዓል የሚከበርበት ወቅት አስደሳች እንዲሆንላችሁ አድርጉ!” በሚለው ርዕስ ሥር በቀረቡ አንዳንድ አስፈላጊ ነጥቦች ላይ ተወያዩ። (km 2/14 2) ቀደም ብሎ ዕቅድ ማውጣት ምን ያህል አስፈላጊ እንደሆነ ጎላ አድርገህ ግለጽ። (ምሳሌ 21:5) ቀደም ሲል ረዳት አቅኚ ሆነው ላገለገሉ ሁለት አስፋፊዎች ቃለ መጠይቅ አድርግ። ምን መሰናክሎችን ማሸነፍ ጠይቆባቸዋል? ምን አስደሳች በረከቶችንስ አግኝተዋል?
የጉባኤ የመጽሐፍ ቅዱስ ጥናት፦ ia ምዕ. 3 አን. 14-21፤ “በመጽሐፍ ቅዱስ የዘመን አቆጣጠር ውስጥ ትልቅ ቦታ የሚሰጠው ዕለት” የሚለው ሣጥን እና ክለሳ (30 ደቂቃ)
ክለሳና የቀጣዩ ሳምንት ማስተዋወቂያ (3 ደቂቃ)
መዝሙር 135 እና ጸሎት