በቀጥታ ወደ ዋናው ጉዳይ ግባ

በቀጥታ ወደ ርዕስ ማውጫው ሂድ

ክርስቲያናዊ ሕይወት

ክልላችሁ ውስጥ ያሉትን ሰዎች ሁሉ በመታሰቢያው በዓል ላይ እንዲገኙ ጋብዙ!

ክልላችሁ ውስጥ ያሉትን ሰዎች ሁሉ በመታሰቢያው በዓል ላይ እንዲገኙ ጋብዙ!

የካቲት 27 በሚጀመረው ዘመቻ አማካኝነት በተቻለ መጠን በአካባቢያችን ያሉ በርካታ ሰዎች የክርስቶስን ሞት መታሰቢያ ከእኛ ጋር እንዲያከብሩ እንጋብዛለን። በተጨማሪም ፍላጎት ያሳዩ ሰዎችን ተመልሰን ሄደን ለመርዳት ልዩ ጥረት እናደርጋለን።

ልንወስዳቸው የሚገቡ እርምጃዎች

መልእክቱን መናገር

“ሰዎች መጋቢት 14 (እንደ አውሮፓውያን አቆጣጠር መጋቢት 23) በሚከበር አንድ ልዩ በዓል ላይ እንዲገኙ የጥሪ ወረቀት እየሰጠን ነው። በዚህ ዕለት በዓለም ዙሪያ ያሉ በሚሊዮን የሚቆጠሩ ሰዎች የኢየሱስ ክርስቶስን ሞት መታሰቢያ በዓል ለማክበር ይሰበሰባሉ፤ በዚያ ቀን፣ ከኢየሱስ ሞት ጥቅም ማግኘት የምንችለው እንዴት እንደሆነ የሚያብራራ ንግግር ይቀርባል። ይህ የጥሪ ወረቀት ስብሰባው በአካባቢያችን የሚደረገው የትና በስንት ሰዓት እንደሆነ ይገልጻል። የሚችሉ ከሆነ ቢመጡ ደስ ይለናል።”

ግለሰቡ ፍላጎት እንዳለው ካሳየ . . .

  • መጠበቂያ ግንብ አበርክት

    ተመላልሶ መጠይቅ ለማድረግ መሠረት ጣል።

  • ስለ መታሰቢያው በዓል የሚገልጸውን ቪዲዮ አሳይ

    ተመላልሶ መጠይቅ ለማድረግ መሠረት ጣል።

ተመላልሶ መጠይቅ ለማድረግ ስትሄድ . . .

  • መጽሐፍ ቅዱስን መማር የሚኖርብን ለምንድን ነው? የተባለውን ቪዲዮ አሳይ

    የማስጠኛ ጽሑፍ አበርክት።

  • ትክክለኛው የመጽሐፍ ቅዱስ ትምህርት ምንድን ነው? የተባለውን መጽሐፍ አበርክት

    ከገጽ 206-208 ላይ ያሉትን ሐሳቦች በመጠቀም ስለ መታሰቢያው በዓል ተጨማሪ መረጃ አካፍለው። ከዚያም መጽሐፉን አበርክት።

  • አምላክን ስማ የተባለውን ብሮሹር አበርክት

    ከገጽ 18-19 ላይ ባሉት ሐሳቦች በመጠቀም የክርስቶስ ሞት ምን ትርጉም እንዳለው አብራራ። ከዚያም ብሮሹሩን አበርክት።