በቀጥታ ወደ ዋናው ጉዳይ ግባ

በቀጥታ ወደ ርዕስ ማውጫው ሂድ

ከአምላክ ቃል የሚገኝ ውድ ሀብት | አስቴር 1–5

አስቴር ለአምላክ ሕዝቦች ጥብቅና ቆማለች

አስቴር ለአምላክ ሕዝቦች ጥብቅና ቆማለች

አስቴር የአምላክን ሕዝብ ለመታደግ የወሰደችው እርምጃ አስደናቂ እምነትና ድፍረት እንዳላት ያሳያል

  • ንጉሡ ፊት ሳይጠሩ መቅረብ ሞት ያስከትላል። አስቴር ደግሞ ለ30 ቀን ያህል ንጉሡ ወደ እሱ እንድትመጣ አልጋበዛትም ነበር

  • ንጉሥ አሐሽዌሮስ (ቀዳማዊ ጠረክሲስ እንደሆነ ይታሰባል) በቀላሉ የሚበሳጭ ሰው ነው። በአንድ ወቅት አንድ ሰው ሁለት ቦታ እንዲሰነጠቅና ለመቀጣጫነት ሌሎች እንዲያዩት ትእዛዝ አስተላልፎ ነበር። አስጢንም እሱን ለመታዘዝ ፈቃደኛ ባለመሆኗ ከንግሥናዋ ሽሯታል

  • አስቴር አይሁዳዊት መሆኗን መናገርና ንጉሡ የሚያምነው ሰው እንዳታለለው ማሳመን ይጠበቅባታል