በቀጥታ ወደ ዋናው ጉዳይ ግባ

በቀጥታ ወደ ርዕስ ማውጫው ሂድ

የካቲት 8-14

ነህምያ 5-8

የካቲት 8-14
  • መዝሙር 123 እና ጸሎት

  • የመግቢያ ሐሳብ (3 ደቂቃ ወይም ከዚያ በታች)

ከአምላክ ቃል የሚገኝ ውድ ሀብት

በአገልግሎት ውጤታማ ለመሆን ተጣጣር

  • መመሥከር፦ (2 ደቂቃ ወይም ከዚያ በታች) የሽፋን ርዕሱን በመጠቀም በቅርቡ የደረሰንን ንቁ! መጽሔት አበርክት። ለተመላልሶ መጠየቅ መሠረት ጣል።

  • ተመላልሶ መጠየቅ፦ (4 ደቂቃ ወይም ከዚያ በታች) በቅርቡ በደረሰን ንቁ! መጽሔት የሽፋን ርዕስ ተጠቅመን ስናነጋግረው ፍላጎት ላሳየ ሰው እንዴት ተመላልሶ መጠየቅ ማድረግ እንደሚቻል አሳይ። ለቀጣዩ ተመላልሶ መጠየቅ መሠረት ጣል።

  • የመጽሐፍ ቅዱስ ጥናት፦ (6 ደቂቃ ወይም ከዚያ በታች) የመጽሐፍ ቅዱስ ጥናት እንዴት እንደሚመራ አሳይ። (bh 28-29 አን. 4-5)

ክርስቲያናዊ ሕይወት

  • መዝሙር 62

  • ‘ለመልካም ሥራ እየተጣጣርክ’ ነው?፦ (15 ደቂቃ) በመስከረም 15, 2014 መጠበቂያ ግንብ ከገጽ 3-6 ላይ ተመሥርቶ በሽማግሌ የሚቀርብ ንግግር። ወንድሞች ለመልካም ሥራ ተጣጣሩ! የተባለውን በታኅሣሥ 2015 JW ብሮድካስት ላይ የወጣውን ቪዲዮ አሳይ። ለመልካም ሥራ ለመጣጣር የሚያነሳሳን ትክክለኛ ምክንያት ምን እንደሆነ እንዲሁም አንድ ወንድም ይህን ማድረግ የሚችለው እንዴት እንደሆነ ጎላ አድርገህ ግለጽ። ወንድሞች የጉባኤ አገልጋይ ወይም ሽማግሌ ሆነው ለማገልገል የሚያስችላቸውን ብቃት ለማሟላት ጥረት እንዲያደርጉ በደግነት አበረታታ።

  • የጉባኤ የመጽሐፍ ቅዱስ ጥናት፦ ia ምዕ. 4 አን. 1-15፤ “እጥር ምጥን ያለ ድንቅ የሥነ ጽሑፍ ሥራ” የሚለው ሣጥን (30 ደቂቃ)

  • ክለሳና የቀጣዩ ሳምንት ማስተዋወቂያ (3 ደቂቃ)

  • መዝሙር 125 እና ጸሎት