አንዲት ወጣት እህት ያዘጋጀችውን ጽሑፍ በክፍሏ ተማሪዎች ፊት ስታቀርብ

የክርስቲያናዊ ሕይወትና አገልግሎት ስብሰባ አስተዋጽኦ የካቲት 2017

የአቀራረብ ናሙናዎች

ለንቁ! መጽሔት እንዲሁም ስለ ሕይወት አመጣጥ እውነቱን ለማስተማር የተዘጋጁ የአቀራረብ ናሙናዎች። ናሙናዎቹን ተጠቅመህ የራስህን መግቢያ አዘጋጅ።

ከአምላክ ቃል የሚገኝ ውድ ሀብት

ይሖዋን መታዘዝ በረከት ያስገኛል

ይሖዋ ሕይወታችንን እንዴት መምራት እንዳለብን ያስተምረናል፤ ይህን የሚያደርገው ስለሚወደን ነው።

ከአምላክ ቃል የሚገኝ ውድ ሀብት

ክርስቶስ ስለ እኛ መከራ ተቀብሏል

የኢየሱስ ሞት፣ ሰይጣን የአምላክን አገልጋዮች ታማኝነት አስመልክቶ ላነሳው ግድድር መልስ አስገኝቷል።

ክርስቲያናዊ ሕይወት

ልጆቻችሁ በፈጣሪ ላይ የማይናወጥ እምነት እንዲያዳብሩ እርዷቸው

ልጆቻችሁ ስለ ሕይወት አመጣጥ ምን ብለው ያምናሉ? ሁሉን የፈጠረው ይሖዋ እንደሆነ እንዲያምኑ ልትረዷቸው የምትችሉት እንዴት ነው?

ከአምላክ ቃል የሚገኝ ውድ ሀብት

‘ይሖዋ በጎ ፈቃድ የሚያሳይበትን ዓመት አውጁ’

ይሖዋ በጎ ፈቃድ የሚያሳይበት ዓመት ቃል በቃል የአንድ ዓመት ርዝማኔ ያለውን ጊዜ የሚያመለክት ነው? ይህ ጊዜ ከመንግሥቱ ስብከት ሥራ ጋር የሚያያዘው እንዴት ነው?

ክርስቲያናዊ ሕይወት

መጽሐፍ ቅዱሳዊ ጽሑፎቻችንን በአግባቡ ተጠቀሙባቸው

መጽሐፍ ቅዱሳዊ ጽሑፎቻችንን ማተምና በዓለም ዙሪያ ወደሚገኙ ጉባኤዎች ማጓጓዝ ከፍተኛ ድካምና ወጪ ይጠይቃል። በመሆኑም ጽሑፎቻችንን ለሌሎች ስታበረክቱ አስተዋዮች ሁኑ።

ከአምላክ ቃል የሚገኝ ውድ ሀብት

አዲስ ሰማያትና አዲስ ምድር ታላቅ ደስታ ያስገኛሉ

አምላክ “አዲስ ሰማያትና አዲስ ምድር” እንደሚያመጣ የገባው ቃል ለእኛ ምን ትርጉም አለው?

ክርስቲያናዊ ሕይወት

በተስፋችሁ ደስ ይበላችሁ

ተስፋ ልክ እንደ መልሕቅ ነው። በአምላክ ቃል ውስጥ በሚገኙት ተስፋዎች ላይ ማሰላሰላችን እንደ ማዕበል ያለ ከባድ ሁኔታ በሚያጋጥመን ጊዜ ደስታችንንና ንጹሕ አቋማችንን ጠብቀን እንድንቀጥል ይረዳናል።