ክርስቲያናዊ ሕይወት
ልጆቻችሁ በፈጣሪ ላይ የማይናወጥ እምነት እንዲያዳብሩ እርዷቸው
ፍጥረት የይሖዋን ክብር ይናገራል። (መዝ 19:1-4፤ 139:14) ሆኖም ዲያብሎስ የሚቆጣጠረው ዓለም የሕይወትን አመጣጥ በተመለከተ አምላክን የሚያቃልሉ ጽንሰ ሐሳቦችን ያስፋፋል። (ሮም 1:18-25) ታዲያ እንዲህ ያሉት ሐሳቦች በልጆቻችሁ አእምሮና ልብ ላይ ተጽዕኖ እንዳያሳድሩ መከላከል የምትችሉት እንዴት ነው? ከሕፃንነታቸው ጀምራችሁ ይሖዋ እንዳለና በግለሰብ ደረጃ እንደሚያስብላቸው እምነት እንዲያዳብሩ እርዷቸው። (2ቆሮ 10:4, 5፤ ኤፌ 6:16) በትምህርት ቤት ስለሚማሩት ነገር ምን አመለካከት እንዳላቸው ለማወቅ ሞክሩ፤ እንዲሁም የይሖዋ ድርጅት ያዘጋጃቸውን በርካታ መሣሪያዎች በመጠቀም ልባቸውን ለመንካት ጥረት አድርጉ።—ምሳሌ 20:5፤ ያዕ 1:19
እኩዮችህ ምን ይላሉ?—በአምላክ ማመን የተባለውን ቪዲዮ አጫውት፤ ከዚያም በሚከተሉት ጥያቄዎች ላይ ተወያዩ፦
ብዙዎች በአምላክ ማመንን በተመለከተ ምን የተሳሳተ አመለካከት አላቸው?
በትምህርት ቤታችሁ ስለዚህ ጉዳይ ምን ትምህርት ይሰጣል?
ይሖዋ መኖሩን እንድታምኑ ያደረጋችሁ ምንድን ነው?
አንድ ሰው፣ ሁሉንም ነገር የፈጠረው አምላክ እንደሆነ እንዲገነዘብ ልትረዱት የምትችሉት እንዴት ነው?