ክርስቶስ ስለ እኛ መከራ ተቀብሏል
“ሰዎች የናቁትና ያገለሉት [ነበር] . . . እንደተቀሰፈ፣ በአምላክ እንደተመታና እንደተጎሳቆለ አድርገን ቆጠርነው”
-
ኢየሱስ በሰዎች ተንቋል፤ እንዲሁም ‘አምላክን ሰድበሃል’ የሚል ክስ ተሰንዝሮበታል። አንዳንዶች አምላክ በአሰቃቂ በሽታ እንዲሠቃይ በማድረግ እየቀጣው እንዳለ ተሰምቷቸው ነበር
“እሱን ማድቀቅ የይሖዋ ፈቃድ ነበር . . . በእሱ አማካኝነት ይሖዋ ደስ የሚሰኝበት ነገር ይከናወናል”
-
ይሖዋ፣ ልጁ ሲገደል ማየቱ የስሜት ሥቃይ አስከትሎበት እንደሚሆን ጥርጥር የለውም። ነገር ግን ኢየሱስ የማይናወጥ ታማኝነት እንዳሳየ ሲመለከት ተደስቷል። የኢየሱስ ሞት፣ ሰይጣን የአምላክ አገልጋዮችን ታማኝነት በተመለከተ ላስነሳው ግድድር መልስ ሰጥቷል፤ እንዲሁም ንስሐ ለሚገቡ የሰው ልጆች በረከት አስገኝቷል። በዚህ መንገድ “የይሖዋ ፈቃድ” እንዲፈጸም አድርጓል