በቀጥታ ወደ ዋናው ጉዳይ ግባ

በቀጥታ ወደ ርዕስ ማውጫው ሂድ

ከአምላክ ቃል የሚገኝ ውድ ሀብት | ኢሳይያስ 58-62

‘ይሖዋ በጎ ፈቃድ የሚያሳይበትን ዓመት አውጁ’

‘ይሖዋ በጎ ፈቃድ የሚያሳይበትን ዓመት አውጁ’

‘ይሖዋ በጎ ፈቃድ የሚያሳይበት ዓመት’ ቃል በቃል የአንድ ዓመት ርዝማኔ ያለውን ጊዜ የሚያመለክት አይደለም

61:1, 2

  • ይህ “ዓመት” ይሖዋ ቅን ልብ ያላቸው ሰዎች እሱ ለሚያሳውጀው የነፃነት አዋጅ አዎንታዊ ምላሽ መስጠት የሚችሉበት አጋጣሚ እንዲያገኙ ሲል የፈቀደውን ጊዜ ያመለክታል

  • በመጀመሪያው መቶ ዘመን ይህ የበጎ ፈቃድ ዓመት የጀመረው ኢየሱስ በ29 ዓ.ም. አገልግሎቱን በጀመረበት ወቅት ሲሆን በ70 ዓ.ም. ኢየሩሳሌም በይሖዋ ‘የበቀል ቀን’ እስከጠፋችበት ጊዜ ድረስ ቀጥሏል

  • በዘመናችን የበጎ ፈቃድ ዓመት የጀመረው በ1914 ኢየሱስ በሰማይ በነገሠበት ጊዜ ሲሆን የሚደመደመው ደግሞ በታላቁ መከራ ነው

ይሖዋ ሕዝቦቹን “ትላልቅ የጽድቅ ዛፎች” በመስጠት ይባርካቸዋል

61:3, 4

  • በዓለም ላይ የሚገኙት ረጃጅም ዛፎች በአብዛኛው የሚያድጉት ጫካ ውስጥ ነው፤ ጫካ ውስጥ ያሉ ዛፎች እርስ በርስ ይደጋገፋሉ

  • ሥሮቻቸው እርስ በርስ ስለሚጠላለፉ ዛፎቹ ኃይለኛ ነፋስም እንኳ መቋቋም ይችላሉ

  • ረጃጅሞቹ ዛፎች ለችግኞቹ ጥላ ይሆኗቸዋል፤ እንዲሁም ከዛፎቹ ላይ የሚረግፉት ቅጠሎች ከሥር ላለው አፈር ለምነት ይጨምሩለታል

የዓለም አቀፉ ክርስቲያን ጉባኤ አባላት በሙሉ “ትላልቅ የጽድቅ ዛፎች” የሆኑት ቅቡዓን ቀሪዎች ከሚሰጡት ድጋፍና ጥበቃ ጥቅም ያገኛሉ