ክርስቲያናዊ ሕይወት
በተስፋችሁ ደስ ይበላችሁ
ተስፋ እንደ መልሕቅ ነው። (ዕብ 6:19) በሕይወታችን ውስጥ እንደ ማዕበል ያለ ከባድ ሁኔታ ሲያጋጥመን ባሕር ላይ አደጋ ደርሶበት እንደተሰባበረ መርከብ እምነታችን እንዳይጠፋ ይረዳናል። (1ጢሞ 1:18, 19) እንደ ማዕበል ሊሆኑብን ከሚችሉ ነገሮች መካከል በሠራነው ስህተት የተነሳ የሚሰማን የተስፋ መቁረጥ ስሜት፣ ቁሳዊ ንብረትን ማጣት፣ ለረጅም ጊዜ የዘለቀ ሕመም፣ የምንወደውን ሰው በሞት ማጣት ወይም ንጹሕ አቋማችንን አደጋ ላይ የሚጥል ማንኛውም ፈተና ሊሆን ይችላል።
እምነትና ተስፋ፣ ቃል የተገባልን ሽልማት ፍንትው ብሎ እንዲታየን ያደርጋሉ። (2ቆሮ 4:16-18፤ ዕብ 11:13, 26, 27) ስለሆነም ተስፋችን በሰማይ መኖርም ይሁን በምድር በአምላክ ቃል ውስጥ በተገለጹት ተስፋዎች ላይ በማሰላሰል ተስፋችንን አጠንክረን መያዝ ይኖርብናል። እንዲህ ካደረግን፣ ፈተናዎች ሲያጋጥሙን ደስታችንን ጠብቀን መኖር እንችላለን። —1ጴጥ 1:6, 7
በተስፋው ደስ ይበላችሁ የተባለውን ቪዲዮ ተመልከቱ፤ ከዚያም የሚከተሉትን ጥያቄዎች ለመመለስ ሞክሩ፦
-
ሙሴ ልንከተለው የሚገባ ጥሩ ምሳሌ የተወልን እንዴት ነው?
-
የቤተሰብ ራሶች ምን ኃላፊነት አለባቸው?
-
በቤተሰብ አምልኳችሁ ላይ የትኞቹን ርዕሰ ጉዳዮች ልታካትቱ ትችላላችሁ?
-
ተስፋ፣ ፈተናዎችን በልበ ሙሉነት እንድንጋፈጥ የሚረዳን እንዴት ነው?
-
በጉጉት የምትጠብቀው ተስፋ የትኛው ነው?