አዲስ ሰማያትና አዲስ ምድር ታላቅ ደስታ ያስገኛሉ
በኢሳይያስ ምዕራፍ 65 ላይ ተመዝግቦ የሚገኘው አምላክ የተናገረው የተሃድሶ ተስፋ መፈጸሙ በጣም የተረጋገጠ ከመሆኑ የተነሳ ይሖዋ ልክ እንደተፈጸመ አድርጎ ተናግሯል።
65:17
ይሖዋ ያለፉት ነገሮች የማይታሰቡበት አዲስ ሰማያትና አዲስ ምድር ይፈጥራል
አዲሶቹ ሰማያት ምንድን ናቸው?
-
በምድር ላይ ጽድቅ እንዲሰፍን የሚያደርግ አዲስ መስተዳድር
-
ይህ መስተዳድር የተቋቋመው፣ በ1914 ክርስቶስ የአምላክ መንግሥት ንጉሥ ሆኖ ዙፋኑን በተረከበበት ወቅት ነው
አዲሱ ምድር ምንድን ነው?
-
ከሁሉም ብሔር፣ ቋንቋና ጎሳ የተውጣጡና በሰማይ ለተቋቋመው አዲስ መስተዳድር በፈቃደኝነት የሚገዙ ሰዎችን ያቀፈ ማኅበረሰብ
“የቀድሞዎቹ ነገሮች አይታሰቡም” ሲባል ምን ማለት ነው?
-
መጥፎ ትዝታ እንዲኖረን የሚያደርግ አካላዊ፣ አእምሯዊና ስሜታዊ ሥቃይ በሙሉ ይወገዳል
-
ታማኝ የሆኑ የሰው ልጆች በሕይወታቸው ሙሉ በሙሉ ደስተኞች ይሆናሉ፤ እያንዳንዱ ቀን ባለፈ ቁጥር አስደሳች ትዝታ ይኖራቸዋል