በቀጥታ ወደ ዋናው ጉዳይ ግባ

በቀጥታ ወደ ርዕስ ማውጫው ሂድ

የአቀራረብ ናሙናዎች

የአቀራረብ ናሙናዎች

ንቁ!

ጥያቄ፦ የመንፈስ ጭንቀት ያለባቸው በአሥራዎቹ ዕድሜ ላይ የሚገኙ ወጣቶች ቁጥር በአስደንጋጭ ሁኔታ እየጨመረ ነው። ይህን ችግር በተመለከተ ማድረግ የምንችለው ነገር ያለ ይመስልሃል?

አበርክት፦ ይህ መጽሔት በአሥራዎቹ ዕድሜ ላይ የሚገኙ ወጣቶች የመንፈስ ጭንቀትን መቋቋም የሚችሉት እንዴት እንደሆነና ወላጆች የመንፈስ ጭንቀት ያለባቸውን ልጆቻቸውን መርዳት የሚችሉት እንዴት እንደሆነ አንዳንድ ምክሮችን ይሰጣል።

እውነትን አስተምሩ

ጥያቄ፦ የትዳር ሕይወትን አስደሳች ማድረግ የሚቻለው እንዴት ነው?

ጥቅስ፦ ኤፌ 5:33

እውነት፦ የትዳር ሕይወት አስደሳች ሊሆን የሚችለው በፍቅርና በአክብሮት ላይ የተገነባ ሲሆን ነው።

የሕይወት አመጣጥ—መልስ የሚያሻቸው አምስት ጥያቄዎች (lf)

ጥያቄ፦ ‘ሕይወት የተገኘው ከየት ነው?’ እንደሚለው ላሉ አስፈላጊ ጥያቄዎች እምነት የሚጣልበት መልስ ከየት ማግኘት የሚቻል ይመስልሃል?

ጥቅስ፦ ዕብ 11:1

አበርክት፦ ይህ ጥቅስ እንደሚናገረው እምነታችን ‘በተጨባጭ ማስረጃ’ ላይ የተመሠረተ መሆን አለበት። ይህ ብሮሹር የሕይወትን አመጣጥ በተመለከተ የሚነሱ አምስት ወሳኝ ጥያቄዎችን ይዟል፤ በተጨማሪም አስተማማኝ ከሆኑ ማስረጃዎች በመነሳት ምን መደምደሚያ ላይ መድረስ እንደሚቻል ይናገራል።

የራስህን መግቢያ አዘጋጅ

ከላይ የተጠቀሱትን ምሳሌዎች እንደ ናሙና አድርገህ በመጠቀም በመስክ አገልግሎት ላይ የምትጠቀምበት የራስህን አቀራረብ አዘጋጅ።