የክርስቲያናዊ ሕይወትና አገልግሎት ስብሰባ አስተዋጽኦ የካቲት 2018
የውይይት ናሙናዎች
‘የመጽሐፍ ቅዱስ መመሪያዎች ጊዜ ያለፈባቸው ይመስልሃል? መጽሐፍ ቅዱስ ከሳይንስ ጋር ይስማማል? መጽሐፍ ቅዱስ ጠቃሚ ምክር ይዟል?’ በሚሉት ጥያቄዎች ላይ የተመሠረቱ ውይይቶች።
ከአምላክ ቃል የሚገኝ ውድ ሀብት
የስንዴውና የእንክርዳዱ ምሳሌ
ኢየሱስ የስንዴውንና የእንክርዳዱን ምሳሌ የተናገረው ምን ለማስተማር ፈልጎ ነው? ዘሪው፣ ጠላቱ፣ እንዲሁም አጫጆቹ ማንን ይወክላሉ?
ክርስቲያናዊ ሕይወት
ስለ መንግሥቱ የሚገልጹ ምሳሌዎች ለእኛ ምን ትርጉም አላቸው?
ኢየሱስ ቀላል በሆኑ ምሳሌዎች ተጠቅሞ ጥልቀት ያላቸውን መንፈሳዊ ትምህርቶች አስተምሯል። ከማቴዎስ ምዕራፍ 13 ምን ተጨማሪ ትምህርቶች እናገኛለን?
ከአምላክ ቃል የሚገኝ ውድ ሀብት
በጥቂቶች ተጠቅሞ ብዙኃኑን መመገብ
የኢየሱስ ደቀ መዛሙርት ከአምስት ዳቦና ከሁለት ዓሣ በቀር ምንም ያልነበራቸው ቢሆንም ኢየሱስ በሺዎች የሚቆጠሩ ሰዎችን እንዲመግቡ አዟቸዋል። በወቅቱ ምን ተአምር ተከናወነ? ይህስ ለእኛ ምን ትርጉም አለው?
ክርስቲያናዊ ሕይወት
“አባትህንና እናትህን አክብር”
ኢየሱስ ‘አባትህንና እናትህን አክብር’ ለሚለው ትእዛዝ አጽንኦት ሰጥቶ ተናግሯል። ወላጆቻችንን እንድናከብር የተሰጠን ትእዛዝ የጊዜ ገደብ አለው?
ከአምላክ ቃል የሚገኝ ውድ ሀብት
የምታስቡት የማንን ሐሳብ ነው?
በአምላክ አስተሳሰብ ለመመራት ምን ማድረግ ይኖርብናል? ኢየሱስ የተሳሳተ አስተሳሰብን ለማስወገድ የሚረዱ ሦስት ነገሮችን ጠቅሷል።
ክርስቲያናዊ ሕይወት
በአገልግሎት ረገድ ክህሎታችንን ማዳበር—ጥያቄዎችን ውጤታማ በሆነ መንገድ መጠቀም
ኢየሱስ ያዳምጡት ለነበሩት ሰዎች የተለያዩ ትምህርቶችን ለማስተማር ጥያቄዎችን ውጤታማ በሆነ መንገድ ተጠቅሟል። በአገልግሎታችን የኢየሱስን ውጤታማ የማስተማሪያ ዘዴ መኮረጅ የምንችለው እንዴት ነው?
ከአምላክ ቃል የሚገኝ ውድ ሀብት
ራሳችሁንም ሆነ ሌሎችን እንዳታሰናክሉ ተጠንቀቁ
ኢየሱስ መሰናከልም ሆነ ሌሎችን ማሰናከል ምን ያህል ከባድ እንደሆነ ለማስተማር ምሳሌዎችን ተጠቅሟል። በሕይወትህ ውስጥ ምን ነገር መሰናክል ሊሆንብህ ይችላል?