በቀጥታ ወደ ዋናው ጉዳይ ግባ

በቀጥታ ወደ ርዕስ ማውጫው ሂድ

ከአምላክ ቃል የሚገኝ ውድ ሀብት | ማቴዎስ 14-15

በጥቂቶች ተጠቅሞ ብዙኃኑን መመገብ

በጥቂቶች ተጠቅሞ ብዙኃኑን መመገብ

በ32 ዓ.ም. የፋሲካ በዓል ከመከበሩ ጥቂት ቀደም ብሎ ኢየሱስ አንድ ተአምር ፈጸመ፤ አራቱም የወንጌል ጸሐፊዎች የዘገቡት ብቸኛው ተአምር ይህ ነው።

በዚህ ተአምር አማካኝነት ኢየሱስ በዛሬው ጊዜም ብዙኃኑን ለመመገብ ምን ዓይነት ዘዴ እንደሚጠቀም አሳይቷል።

14:16-21

  • ደቀ መዛሙርቱ ከአምስት ዳቦና ከሁለት ዓሣ በቀር ምንም ያልነበራቸው ቢሆንም ኢየሱስ እዚያ የተሰበሰበውን ሕዝብ እንዲመግቡ አዟቸዋል

  • ኢየሱስ ዳቦውንና ዓሣውን ይዞ ከጸለየ በኋላ ቆርሶ ለደቀ መዛሙርቱ ሰጣቸው፤ ደቀ መዛሙርቱ ደግሞ ለሕዝቡ አከፋፈሉ

  • ተአምራዊ በሆነ መንገድ ምግቡ ለሁሉም ሰው ተዳርሶ ተረፈ። ኢየሱስ በጥቂቶች ማለትም በደቀ መዛሙርቱ ተጠቅሞ በሺዎች የሚቆጠሩ ሰዎችን መግቧል

  • ኢየሱስ በመጨረሻዎቹ ቀናት ‘በተገቢው ጊዜ ምግብ’ የሚያቀርብ ባሪያ እንደሚሾም አስቀድሞ ተናግሯል።—ማቴ 24:45

  • በ1919 ኢየሱስ ‘ታማኝና ልባም ባሪያን’ ማለትም ጥቂት የተቀቡ ወንድሞችን ያቀፈውን ቡድን “በቤተሰቦቹ” ላይ ማለትም ምግቡን በሚመገቡት ላይ ሾሟል

  • ኢየሱስ ጥቂት የተቀቡ ወንድሞችን ባቀፈው በዚህ ቡድን አማካኝነት ብዙኃኑን በመመገብ በመጀመሪያው መቶ ዘመን የተጠቀመበትን ዘዴ በዛሬው ጊዜም እየተጠቀመ ነው

ኢየሱስ ሰዎችን በመንፈሳዊ ለመመገብ የሚጠቀምበትን መስመር እንደምቀበልና እንደማከብር ማሳየት የምችለው እንዴት ነው?