በቀጥታ ወደ ዋናው ጉዳይ ግባ

በቀጥታ ወደ ርዕስ ማውጫው ሂድ

ክርስቲያናዊ ሕይወት

“አባትህንና እናትህን አክብር”

“አባትህንና እናትህን አክብር”

ኢየሱስ ምድር ላይ በነበረበት ወቅት “አባትህንና እናትህን አክብር” የሚለውን ትእዛዝ የመጠበቅን አስፈላጊነት አጉልቶ ተናግሯል። (ዘፀ 20:12፤ ማቴ 15:4) ኢየሱስ እንዲህ ብሎ ለመናገር ነፃነት እንደሚሰማው እርግጠኞች መሆን እንችላለን፤ ምክንያቱም ልጅ ሳለ ወላጆቹን “ይታዘዛቸው” ነበር። (ሉቃስ 2:51 ግርጌ) አዋቂ ከሆነ በኋላም ለእናቱ አሳቢነት አሳይቷል፤ እሱ ከሞተ በኋላ እናቱን የሚንከባከብ ሰው እንዲኖር ዝግጅት አድርጓል።—ዮሐ 19:26, 27

በዛሬው ጊዜ ያሉ ክርስቲያን ልጆችም ለወላጆቻቸው በመታዘዝና እነሱን በአክብሮት በማነጋገር ወላጆቻቸውን እንደሚያከብሩ ያሳያሉ። ደግሞም ወላጆቻችንን እንድናከብር የተሰጠን ትእዛዝ የጊዜ ገደብ የለውም። ወላጆቻችን በዕድሜ ከገፉ በኋላም እንኳ፣ የሚሰጡንን ጥበብ ያዘለ ምክር በመስማት ለእነሱ አክብሮት ማሳየታችንን መቀጠል ይኖርብናል። (ምሳሌ 23:22) በተጨማሪም እንደ አስፈላጊነቱ ስሜታዊና ቁሳዊ ድጋፍ በማድረግ በዕድሜ የገፉ ወላጆቻችንን እንደምናከብር ማሳየት እንችላለን። (1ጢሞ 5:8) ልጆችም ሆን አዋቂዎች ወላጆቻችንን እንደምናከብር የምናሳይበት ዋነኛው መንገድ ከእነሱ ጋር ጥሩ የሐሳብ ግንኙነት እንዲኖረን በማድረግ ነው።

ወላጆቼን ማነጋገር የምችለው እንዴት ነው? የሚለውን የነጭ ሰሌዳ አኒሜሽን ቪዲዮ ተመልከት፤ ከዚያም የሚከተሉትን ጥያቄዎች ለመመለስ ሞክር፦

  • ወላጆችህን ማነጋገር የሚከብድህ ለምን ሊሆን ይችላል?

  • ወላጆችህን ስታነጋግር ለእነሱ አክብሮት እንዳለህ ማሳየት የምትችለው እንዴት ነው?

  • ወላጆችህን ለማነጋገር ጥረት ማድረግህ የሚክስህ እንዴት ነው? (ምሳሌ 15:22)

    ወላጆችህን ማነጋገርህ በሕይወትህ ስኬታማ እንድትሆን ይረዳሃል