በቀጥታ ወደ ዋናው ጉዳይ ግባ

በቀጥታ ወደ ርዕስ ማውጫው ሂድ

ክርስቲያናዊ ሕይወት

በአገልግሎት ረገድ ክህሎታችንን ማዳበር—ጥያቄዎችን ውጤታማ በሆነ መንገድ መጠቀም

በአገልግሎት ረገድ ክህሎታችንን ማዳበር—ጥያቄዎችን ውጤታማ በሆነ መንገድ መጠቀም

አስፈላጊ የሆነው ለምንድን ነው? “በሰው ልብ ውስጥ ያለ ሐሳብ እንደ ጥልቅ ውኃ” ከሆነ ጥያቄዎች ደግሞ ውኃውን ለመቅዳት እንደምንጠቀምበት ዕቃ ናቸው ማለት ይቻላል። (ምሳሌ 20:5) ጥያቄዎች አድማጫችንን ለማሳተፍ ይረዱናል። ግለሰቡ ላቀረብንለት በሚገባ የታሰበበት ጥያቄ የሚሰጠው መልስ ስለ እሱ ጠቃሚ መረጃ እንድናገኝ ያስችለናል። ኢየሱስ ጥያቄዎችን ውጤታማ በሆነ መንገድ ተጠቅሟል። በዚህ ረገድ የእሱን ምሳሌ መከተል የምንችለው እንዴት ነው?

ይህን ማድረግ የሚቻለው እንዴት ነው?

  • የአመለካከት ጥያቄዎችን ጠይቁ። ኢየሱስ የደቀ መዛሙርቱን አመለካከት ለማወቅ የተለያዩ ጥያቄዎችን ጠይቋቸዋል። (ማቴ 16:13-16be 238 አን. 3-5) እናንተስ የትኞቹን የአመለካከት ጥያቄዎች ልትጠይቁ ትችላላችሁ?

  • መሪ ጥያቄዎችን ጠይቁ። ኢየሱስ የጴጥሮስን አመለካከት ለማስተካከል ጥያቄዎችን ከጠየቀው በኋላ መልስ ሊሆኑ የሚችሉ አማራጮችን አቅርቦለታል፤ ይህም ጴጥሮስ ትክክለኛው ድምዳሜ ላይ እንዲደርስ ረድቶታል። (ማቴ 17:24-26) እናንተስ አንድ ሰው ትክክለኛው ድምዳሜ ላይ እንዲደርስ ለመርዳት የትኞቹን መሪ ጥያቄዎች ልትጠይቁ ትችላላችሁ?

  • አድማጫችሁን አመስግኑ። ኢየሱስ አንድ ጸሐፊ “በማስተዋል እንደመለሰ” በተረዳ ጊዜ አመስግኖታል። (ማር 12:34) አንድ ሰው ለጠየቃችሁት ጥያቄ መልስ ሲሰጥ ልታመሰግኑት የምትችሉት እንዴት ነው?

ኢየሱስ ያከናወነውን ሥራ ሥሩ—ማስተማር የሚለውን ቪዲዮ የመጀመሪያ ክፍል ተመልከት፤ ከዚያም የሚከተሉትን ጥያቄዎች ለመመለስ ሞክር፦

  • ቪዲዮው ላይ ያለው ወንድም ያስተላለፈው መረጃ ትክክል ቢሆንም ጥሩ የማስተማር ዘዴ አልተጠቀመም የምንለው ለምንድን ነው?

  • በምናስተምርበት ጊዜ እንዲሁ መረጃ ማስተላለፋችን ብቻ በቂ ያልሆነው ለምንድን ነው?

የቪዲዮውን ሁለተኛ ክፍል ተመልከት፤ ከዚያም የሚከተሉትን ጥያቄዎች ለመመለስ ሞክር፦

  • ወንድም ጥያቄዎችን ውጤታማ በሆነ መንገድ የተጠቀመው እንዴት ነው?

  • ወንድም ካስተማረበት መንገድ ሌላስ ምን ጠቃሚ ትምህርት እናገኛለን?

የምናስተምርበት መንገድ በሌሎች ላይ ምን ተጽዕኖ ሊያሳድር ይችላል? (ሉቃስ 24:32)