በቀጥታ ወደ ዋናው ጉዳይ ግባ

በቀጥታ ወደ ርዕስ ማውጫው ሂድ

ከየካቲት 26–መጋቢት 4

ማቴዎስ 18–19

ከየካቲት 26–መጋቢት 4
  • መዝሙር 121 እና ጸሎት

  • የመግቢያ ሐሳብ (3 ደቂቃ ወይም ከዚያ በታች)

ከአምላክ ቃል የሚገኝ ውድ ሀብት

  • ራሳችሁንም ሆነ ሌሎችን እንዳታሰናክሉ ተጠንቀቁ”፦ (10 ደቂቃ)

    • ማቴ 18:6, 7—ሌሎችን እንዳናሰናክል መጠንቀቅ አለብን (“የወፍጮ ድንጋይ፣” “የሚያሰናክል ነገር” ለጥናት የሚረዱ መረጃዎች እና “የወፍጮ ድንጋይ፣” “የላይኛውና የታችኛው የወፍጮ ድንጋይ” ሚዲያ—⁠ማቴ 18:6, 7፣ nwtsty)

    • ማቴ 18:8, 9—ሊያሰናክሉን ከሚችሉ ነገሮች ሁሉ መራቅ አለብን (“ገሃነም” ለጥናት የሚረዳ መረጃ—⁠ማቴ 18:9፣ nwtsty እና የቃላት መፍቻ)

    • ማቴ 18:10—ሌሎችን የሚያሰናክል ነገር ስናደርግ ይሖዋ እንደሚያውቅ መገንዘብ ይኖርብናል (“አባቴ ፊት . . . ስለሚቀርቡ” ለጥናት የሚረዳ መረጃ—⁠ማቴ 18:10፣ nwtstyw10 11/1 16)

  • መንፈሳዊ ዕንቁዎችን በምርምር ማግኘት፦ (8 ደቂቃ)

    • ማቴ 18:21, 22—ወንድማችንን ይቅር ለማለት ፈቃደኞች መሆን ያለብን እስከ ስንት ጊዜ ድረስ ነው? (“77 ጊዜ” ለጥናት የሚረዳ መረጃ—⁠ማቴ 18:22፣ nwtsty)

    • ማቴ 19:7—“የፍቺ የምሥክር ወረቀት” ዓላማ ምን ነበር? (“የፍቺ የምሥክር ወረቀት” ለጥናት የሚረዳ መረጃ እና “የፍቺ የምሥክር ወረቀት” ሚዲያ—⁠ማቴ 19:7፣ nwtsty)

    • ከዚህ ሳምንት የመጽሐፍ ቅዱስ ንባብ ስለ ይሖዋ ምን ትምህርት አግኝታችኋል?

    • ከዚህ ሳምንት የመጽሐፍ ቅዱስ ንባብ ምን ሌሎች መንፈሳዊ ዕንቁዎች አግኝታችኋል?

  • የመጽሐፍ ቅዱስ ንባብ፦ (4 ደቂቃ ወይም ከዚያ በታች) ማቴ 18:18-35

በአገልግሎት ውጤታማ ለመሆን ተጣጣር

  • ሁለተኛው ተመላልሶ መጠየቅ፦ (3 ደቂቃ ወይም ከዚያ በታች) የውይይት ናሙናውን ተጠቀም።

  • ሦስተኛው ተመላልሶ መጠየቅ፦ (3 ደቂቃ ወይም ከዚያ በታች) የመረጥከውን ጥቅስ ተጠቀም፤ ከዚያም አንድ የማስጠኛ ጽሑፍ አበርክት።

  • የመጽሐፍ ቅዱስ ጥናት፦ (6 ደቂቃ ወይም ከዚያ በታች) bhs ገጽ 26 አን. 18-20—ልብን መንካት የሚቻለው እንዴት እንደሆነ አሳይ።

ክርስቲያናዊ ሕይወት

  • መዝሙር 90

  • በምንም መንገድ ማሰናከያ አታኑሩ (2ቆሮ 6:3)፦ (9 ደቂቃ) ቪዲዮውን አጫውት።

  • የመታሰቢያው በዓል ዘመቻ መጋቢት 3 ይጀምራል፦ (6 ደቂቃ) በየካቲት 2016 የክርስቲያናዊ ሕይወትና አገልግሎት ስብሰባ አስተዋጽኦ ላይ በወጣው “በክልላችሁ ውስጥ ያሉትን ሰዎች ሁሉ በመታሰቢያው በዓል ላይ እንዲገኙ ጋብዙ!” በሚለው ርዕስ ላይ ተመሥርቶ የሚቀርብ ንግግር። የመታሰቢያው በዓል የመጋበዣ ወረቀት ለሁሉም እንዲሰጥ ካደረግክ በኋላ ስለ ይዘቱ ተናገር። “ኢየሱስ ክርስቶስ በእርግጥ ማን ነው?” የሚል ርዕስ ያለው ልዩ የሕዝብ ንግግሩ የሚቀርበው መጋቢት 19, 2018 በሚጀምረው ሳምንት ላይ እንደሆነ አጽንኦት ሰጥተህ ተናገር። ይህ ንግግር የመታሰቢያውን በዓል በጉጉት እንድንጠባበቅ ለማድረግ ታስቦ የተዘጋጀ ነው። ጉባኤው ክልሉን ለመሸፈን ያደረገውን ዝግጅት ግለጽ።

  • የጉባኤ የመጽሐፍ ቅዱስ ጥናት፦ (30 ደቂቃ) jy ምዕ. 1

  • ክለሳና የቀጣዩ ሳምንት ማስተዋወቂያ (3 ደቂቃ)

  • መዝሙር 96 እና ጸሎት