በቀጥታ ወደ ዋናው ጉዳይ ግባ

በቀጥታ ወደ ርዕስ ማውጫው ሂድ

ከአምላክ ቃል የሚገኝ ውድ ሀብት | ማቴዎስ 18-19

ራሳችሁንም ሆነ ሌሎችን እንዳታሰናክሉ ተጠንቀቁ

ራሳችሁንም ሆነ ሌሎችን እንዳታሰናክሉ ተጠንቀቁ

ኢየሱስ መሰናከልም ሆነ ሌሎችን ማሰናከል ምን ያህል ከባድ እንደሆነ የሚያሳዩ ምሳሌዎችን ተጠቅሟል።

18:6, 7

  • “የሚያሰናክል ነገር” የሚለው አገላለጽ አንድ ሰው የተሳሳተ ጎዳናን እንዲከተል፣ በሥነ ምግባር እንዲሰናከል አሊያም በኃጢአት እንዲወድቅ ምክንያት የሚሆንን ድርጊት ወይም ሁኔታ ያመለክታል

  • አንድን ሰው የሚያሰናክል ግለሰብ የወፍጮ ድንጋይ በአንገቱ ላይ ታስሮ ጥልቅ ባሕር ውስጥ ቢሰጥም ይሻለዋል

የወፍጮ ድንጋዮች

18:8, 9

  • ኢየሱስ ተከታዮቹን እንደ እጅ ወይም ዓይን ያለ ትልቅ ቦታ የሚሰጠው ነገርም እንኳ ማሰናከያ የሚሆንባቸው ከሆነ ሊያስወግዱት እንደሚገባ መክሯቸዋል

  • ትልቅ ቦታ የምንሰጠውን እንዲህ ያለውን ነገር ለመተው ፈቃደኞች ባለመሆናችን ዘላለማዊ ጥፋትን ወደሚያመለክተው ወደ ገሃነም ከምንጣል ይልቅ ይህን ነገር አጥተን ወደ አምላክ መንግሥት መግባት ይሻለናል

በሕይወቴ ውስጥ ማሰናከያ የሚሆንብኝ ነገር ምን ሊሆን ይችላል? ራሴንም ሆነ ሌሎችን ላለማሰናከል መጠንቀቅ የምችለው እንዴት ነው?