በቀጥታ ወደ ዋናው ጉዳይ ግባ

በቀጥታ ወደ ርዕስ ማውጫው ሂድ

ከአምላክ ቃል የሚገኝ ውድ ሀብት | ማቴዎስ 12-13

የስንዴውና የእንክርዳዱ ምሳሌ

የስንዴውና የእንክርዳዱ ምሳሌ

ኢየሱስ የስንዴውንና የእንክርዳዱን ምሳሌ የተናገረው የስንዴውን ክፍል ማለትም ቅቡዓን ክርስቲያኖችን ከመላው የሰው ዘር መካከል የሚሰበስበው እንዴትና መቼ እንደሆነ ለመጠቆም ነው፤ ስንዴው መዘራት የጀመረው በ33 ዓ.ም. ነው።

13:24

‘አንድ ሰው በእርሻው ላይ ጥሩ ዘር ዘራ’

  • ዘሪው፦ ኢየሱስ ክርስቶስ

  • የጥሩው ዘር መዘራት፦ የኢየሱስ ደቀ መዛሙርት በመንፈስ ቅዱስ መቀባት

  • እርሻው፦ የሰው ልጆች ዓለም

13:25

“ሰው ሁሉ ተኝቶ ሳለ ጠላቱ መጥቶ በስንዴው ላይ እንክርዳድ ዘርቶ ሄደ”

  • ጠላት፦ ዲያብሎስ

  • የሰዎቹ መተኛት፦ የሐዋርያት መሞት

13:30

“እስከ መከር ጊዜ ድረስ አብረው ይደጉ”

  • ስንዴው፦ ቅቡዓን ክርስቲያኖች

  • እንክርዳዱ፦ አስመሳይ ክርስቲያኖች

‘በመጀመሪያ እንክርዳዱን ሰብስቡ፤ ከዚያም ስንዴውን ሰብስቡ’

  • ባሪያዎቹ/አጫጆቹ፦ መላእክት

  • የእንክርዳዱ መሰብሰብ፦ የአስመሳይ ክርስቲያኖች ከቅቡዓን ክርስቲያኖች መለየት

  • ወደ ጎተራው ማስገባት፦ የቅቡዓን ክርስቲያኖች እንደገና በተቋቋመው ጉባኤ ውስጥ መሰብሰብ

የመከሩ ወቅት በጀመረበት ጊዜ እውነተኛ ክርስቲያኖችን ከአስመሳይ ክርስቲያኖች ተለይተው እንዲታወቁ ያደረጋቸው ምንድን ነው?

የዚህን ምሳሌ ትርጉም መረዳቴ በግለሰብ ደረጃ የሚጠቅመኝ እንዴት ነው?