በቀጥታ ወደ ዋናው ጉዳይ ግባ

በቀጥታ ወደ ርዕስ ማውጫው ሂድ

ክርስቲያናዊ ሕይወት

ጸንታችሁ በጉጉት ተጠባበቁ

ጸንታችሁ በጉጉት ተጠባበቁ

የአምላክን መንግሥት መምጣት ለምን ያህል ጊዜ ስትጠባበቅ ቆይተሃል? የተለያዩ አስቸጋሪ ሁኔታዎች ቢያጋጥሙህም በጽናት እየተጠባበቅክ ነው? (ሮም 8:25) አንዳንድ ክርስቲያኖች ካጋጠሟቸው ፈተናዎች መካከል ጥላቻ፣ መድልዎ፣ እስራት አልፎ ተርፎም የግድያ ዛቻ ይገኙበታል። ሌሎች ብዙዎች ደግሞ ሥር የሰደደ ሕመም ወይም የዕድሜ መግፋት የሚያስከትሉትን መከራ መቋቋም አስፈልጓቸዋል።

እኛስ መከራ እየደረሰብንም እንኳ በጉጉት ለመጠባበቅ ምን ይረዳናል? በየዕለቱ መጽሐፍ ቅዱስን በማንበብና ባነበብነው ላይ በማሰላሰል እምነታችንን ማጠናከር ያስፈልገናል። በተጨማሪም በተስፋችን ላይ ትኩረት ማድረግ ይኖርብናል። (2ቆሮ 4:16-18፤ ዕብ 12:2) ወደ ይሖዋ ምልጃ ማቅረብ እንዲሁም በመንፈስ ቅዱስ አማካኝነት ኃይል እንዲሰጠን አባታችንን መለመን አለብን። (ሉቃስ 11:10, 13፤ ዕብ 5:7) አፍቃሪው አባታችን “በትዕግሥትና በደስታ ሁሉንም ነገር በጽናት [እንድንቋቋም]” ይረዳናል።—ቆላ 1:11

‘በጽናት ሩጡ’—ሽልማቱን እንደምታገኙ እርግጠኞች ሁኑ የሚለውን ቪዲዮ ተመልከት፤ ከዚያም የሚከተሉትን ጥያቄዎች ለመመለስ ሞክር፦

  • በሕይወታችን ውስጥ የትኞቹ “ያልተጠበቁ ክስተቶች” ሊያጋጥሙን ይችላሉ? (መክ 9:11)

  • መከራዎች ሲያጋጥሙን ጸሎት የሚረዳን እንዴት ነው?

  • ይሖዋን ከዚህ ቀደም እናገለግለው የነበረውን ያህል ማገልገል ባንችል እንኳ አሁን ማድረግ በምንችለው ነገር ላይ ማተኮር ያለብን ለምንድን ነው?

  • ዓይንህ ሽልማቱ ላይ ያተኩር

    ሽልማቱን እንደምታገኝ እርግጠኛ እንድትሆን የሚረዳህ ምንድን ነው?