በቀጥታ ወደ ዋናው ጉዳይ ግባ

በቀጥታ ወደ ርዕስ ማውጫው ሂድ

ክርስቲያናዊ ሕይወት

በአገልግሎት ረገድ ክህሎታችንን ማዳበር—እድገት የማያደርጉ የመጽሐፍ ቅዱስ ተማሪዎችን ማስጠናታችንን ማቆም

በአገልግሎት ረገድ ክህሎታችንን ማዳበር—እድገት የማያደርጉ የመጽሐፍ ቅዱስ ተማሪዎችን ማስጠናታችንን ማቆም

አስፈላጊ የሆነው ለምንድን ነው? ሰዎች መዳን ለማግኘት የይሖዋን ስም መጥራት ይኖርባቸዋል። (ሮም 10:13, 14) እርግጥ ነው፣ መጽሐፍ ቅዱስን ለማጥናት የሚስማሙ ሰዎች ሁሉ በይሖዋ መሥፈርቶች ሕይወታቸውን ለመምራት ፈቃደኛ ይሆናሉ ማለት አይደለም። በመሆኑም ውድ የሆነውን ጊዜያችንን በአግባቡ መጠቀም እንድንችል፣ ይሖዋን ለማስደሰት ሲሉ አስፈላጊውን ለውጥ የማድረግ ልባዊ ፍላጎት ያላቸው ሰዎችን ብቻ መርዳት ይኖርብናል። መጽሐፍ ቅዱስን የምናስጠናው ሰው ከተወሰነ ጊዜ በኋላ ተገቢውን እድገት ካላደረገ ጥናቱን ማቆሙ የጥበብ እርምጃ ነው፤ ጊዜያችንን ይሖዋ ወደ ራሱና ወደ ድርጅቱ የሳባቸውን ሰዎች ለመርዳት ማዋሉ የተሻለ ይሆናል። (ዮሐ 6:44) እርግጥ ነው፣ ግለሰቡ “ወደ ዘላለም ሕይወት የሚመራ ትክክለኛ የልብ ዝንባሌ” እንዳለው ከጊዜ በኋላ ካሳየ እሱን መጽሐፍ ቅዱስ ማስጠናታችንን በደስታ እንቀጥላለን።—ሥራ 13:48

ይህን ማድረግ የሚቻለው እንዴት ነው?

  • ግለሰቡ ትክክለኛ እውቀት ለማግኘት መፈለጉ የሚያስመሰግነው እንደሆነ ግለጽለት።—1ጢሞ 2:4

  • የተማረውን ነገር ተግባራዊ ማድረጉ ምን ያህል አስፈላጊ እንደሆነ ጎላ አድርገህ ግለጽ።—ሉቃስ 6:46-49

  • ኢየሱስ ስለ ዘሪው የተናገረውን ምሳሌ ደግነት በሚንጸባረቅበት መንገድ አብራራለት፤ እንዲሁም እድገት እንዳያደርግ እንቅፋት የሆነበት ምን እንደሆነ ጠይቀው።—ማቴ 13:18-23

  • እሱን ማስጠናትህን የምታቆመው ለምን እንደሆነ በዘዴ አስረዳው

  • አልፎ አልፎ እንደምትጠይቀውና በሕይወቱ ውስጥ ለውጥ ማድረግ ከጀመረ ደግሞ ጥናቱን እንደምትቀጥል ንገረው

ቪዲዮውን ተመልከት፤ ከዚያም የሚከተሉትን ጥያቄዎች ለመመለስ ሞክር፦

  • የመጽሐፍ ቅዱስ ተማሪው መንፈሳዊ እድገት እያደረገ እንዳልሆነ ከአስጠኚው ጋር የሚያደርጉት ውይይት የሚጠቁመው እንዴት ነው?

  • ጥናቱ ለውጥ ማድረግ እንደሚያስፈልገው አስፋፊው ያስረዳው እንዴት ነው?

  • አስፋፊው ለመጽሐፍ ቅዱስ ጥናቱ፣ ወደፊት ጥናታቸውን መቀጠል እንደሚችሉ የጠቆመው እንዴት ነው?