የወይራ ዛፉ ምሳሌ
የምሳሌያዊው የወይራ ዛፍ የተለያዩ ክፍሎች ምን ያመለክታሉ?
-
ዛፉ፦ አምላክ ከአብርሃም ቃል ኪዳን ጋር በተያያዘ ያለውን ዓላማ አፈጻጸም
-
ግንዱ፦ የአብርሃም ዘር ዋነኛ ክፍል የሆነውን ኢየሱስን
-
ቅርንጫፎቹ፦ በአብርሃም ዘር ሁለተኛ ክፍል ውስጥ የሚካተቱትን ሰዎች ሙሉ ቁጥር
-
“የተሰበሩት” ቅርንጫፎች፦ ኢየሱስን ያልተቀበሉትን ሥጋዊ እስራኤላውያን
-
‘የተጣበቁት’ ቅርንጫፎች፦ ከአሕዛብ ወገን የሆኑትን ቅቡዓን ክርስቲያኖች
በትንቢት እንደተነገረው የአብርሃም ዘር ማለትም ኢየሱስና 144,000ዎቹ “ለአሕዛብ በረከት” ያስገኛሉ።—ሮም 11:12፤ ዘፍ 22:18
ይሖዋ ከአብርሃም ዘር ጋር በተያያዘ ያለውን ዓላማ የፈጸመበት መንገድ ስለ እሱ ምን ያስተምረኛል?