በቀጥታ ወደ ዋናው ጉዳይ ግባ

በቀጥታ ወደ ርዕስ ማውጫው ሂድ

ክርስቲያናዊ ሕይወት

የአልኮል መጠጦችን በተመለከተ ጥበብ የሚንጸባረቅበት ውሳኔ አድርጉ

የአልኮል መጠጦችን በተመለከተ ጥበብ የሚንጸባረቅበት ውሳኔ አድርጉ

ሁሉም ክርስቲያኖች ከአልኮል መጠጦች ጋር በተያያዘ ራሳቸውን መግዛት ይኖርባቸዋል። (ምሳሌ 23:20, 29-35፤ 1ቆሮ 6:9, 10) አንድ ክርስቲያን መጠጣት ከወሰነ ከልኩ እንዳያልፍ መጠንቀቅ ይኖርበታል። የአልኮል መጠጥ ሱሰኛ እንዳይሆንና ሌሎችን እንዳያሰናክል መጠንቀቅም አለበት። (1ቆሮ 10:23, 24፤ 1ጢሞ 5:23) ደግሞም ማንንም በተለይ ወጣቶችን እንዲጠጡ መገፋፋት ተገቢ አይደለም።

መጠጣት የሚያስከትለውን መዘዝ አስብ የሚለውን የነጭ ሰሌዳ አኒሜሽን ቪዲዮ ተመልከት፤ ከዚያም የሚከተሉትን ጥያቄዎች ለመመለስ ሞክር፦

  • ሁሉም ክርስቲያኖች ስለ አልኮል መጠጥ የወጡ ሕጎችን መታዘዝ ያለባቸው ለምንድን ነው?—ሮም 13:1-4

  • በሌሎች ግፊት ተሸንፈን መጠጣት የሌለብን ለምንድን ነው?—ሮም 6:16

  • ከመጠጥ ጋር ተያይዘው ከሚመጡ አደገኛ ሁኔታዎች ራሳችንን መጠበቅ የምንችለው እንዴት ነው?