በቀጥታ ወደ ዋናው ጉዳይ ግባ

በቀጥታ ወደ ርዕስ ማውጫው ሂድ

በአገልግሎት ውጤታማ ለመሆን ተጣጣር | በአገልግሎት የምታገኙትን ደስታ አሳድጉ

በግለት ማስተማር

በግለት ማስተማር

ግለት የሚጋባ ነገር ነው። የምናነጋግራቸው ሰዎች በትኩረት እንዲያዳምጡን ሊያደርግ ይችላል። ለምንናገረው መልእክት ምን ያህል ክብደት እንደምንሰጥም ያሳያል። ያደግንበት ባሕል ወይም ባሕርያችን ምንም ይሁን ምን በግለት የማስተማር ችሎታን ማዳበር እንችላለን። (ሮም 12:11) እንዴት?

አንደኛ፣ የምትናገረው መልእክት ምን ያህል አስፈላጊ እንደሆነ አስብ። “የተሻለ ነገር እንደሚመጣ ምሥራች” የማብሰር መብት አግኝተሃል። (ሮም 10:15) ሁለተኛ፣ ምሥራቹ በሰዎች ሕይወት ላይ ምን ያህል ለውጥ እንደሚያመጣ አሰላስል። ሰዎች፣ የምንናገረው መልእክት በጣም ያስፈልጋቸዋል። (ሮም 10:13, 14) በመጨረሻም ሞቅ ባለ ስሜት ተናገር፤ ተስማሚ የሆኑ አካላዊ መግለጫዎችን ተጠቀም፤ ፊትህ ላይ የሚነበበው ነገርም የውስጥህን ስሜት የሚገልጽ ሊሆን ይገባል።

ደቀ መዛሙርት የማድረጉ ሥራ የሚያስገኘውን ደስታ አጣጥሙ—ክህሎታችሁን አሻሽሉ—በግለት ማስተማር የሚለውን ቪዲዮ ተመልከት፤ ከዚያም የሚከተሉትን ጥያቄዎች ለመመለስ ሞክር፦

  • ኒታ፣ ጄድን ስታስጠና ግለቷ እንዲቀዘቅዝ ያደረገው ምንድን ነው?

  • ኒታ ቅንዓቷን መልሳ ለማቀጣጠል የረዳት ምንድን ነው?

  • ግለት የሚጋባ ነገር ነው

    በምናነጋግራቸው ሰዎች አዎንታዊ ጎን ላይ ማተኮር ያለብን ለምንድን ነው?

  • የእኛ ግለት በጥናቶቻችንም ሆነ በሌሎች ላይ ምን ውጤት ሊኖረው ይችላል?