በአገልግሎት ውጤታማ ለመሆን ተጣጣር | በአገልግሎት የምታገኙትን ደስታ አሳድጉ
ቁልፍ ነጥቦችን በምሳሌ ማስረዳት
ተመላልሶ መጠየቅ ስናደርግም ሆነ መጽሐፍ ቅዱስ ስናስጠና፣ የምናነጋግራቸው ሰዎች ቁልፍ ነጥቦችን እንዲያስተውሉ መርዳት ያስፈልገናል። እነዚህን ቁልፍ ነጥቦች ለማስረዳት ምሳሌ መጠቀማችን የሰዎችን ልብ ለመንካትና ትምህርቱን እንዲያስታውሱት ለመርዳት ያስችለናል።
ተመላልሶ መጠየቅ ለማድረግ ወይም ጥናት ለመምራት ስትዘጋጁ በምሳሌ ልታስረዱ የምትፈልጓቸውን ነጥቦች ምረጡ፤ የምትመርጧቸው ነጥቦች ቁልፍ ነጥቦች እንጂ ዝርዝር ሐሳቦች መሆን የለባቸውም። ከዚያም በዕለት ተዕለት ሕይወት ላይ የተመሠረቱ ቀላል ምሳሌዎችን ምረጡ። (ማቴ 5:14-16፤ ማር 2:21፤ ሉቃስ 14:7-11) የግለሰቡን አስተዳደግ ወይም የኋላ ታሪክ እንዲሁም የዕለት ተዕለት እንቅስቃሴውን ግምት ውስጥ አስገቡ። (ሉቃስ 5:2-11፤ ዮሐ 4:7-15) ግለሰቡ ልታስረዱት የፈለጋችሁት ነጥብ ገብቶት ፊቱ በደስታ ሲፈካ ስታዩ እናንተም ትደሰታላችሁ።
ደቀ መዛሙርት የማድረጉ ሥራ የሚያስገኘውን ደስታ አጣጥሙ—ክህሎታችሁን አሻሽሉ—ቁልፍ ነጥቦችን በምሳሌ ማስረዳት የሚለውን ቪዲዮ ተመልከት፤ ከዚያም የሚከተሉትን ጥያቄዎች ለመመለስ ሞክር፦
-
ጥናቶች የመጽሐፍ ቅዱስ ጥቅሶችን ለመረዳት እገዛ የሚያስፈልጋቸው ለምን ሊሆን ይችላል?
-
ኒታ በሮም 5:12 ላይ የሚገኘውን እውነት በምሳሌ ያስረዳችው እንዴት ነው?
-
ጥሩ ምሳሌ በምናነጋግረው ሰው ላይ ምን ውጤት ይኖረዋል?
-
በአገልግሎታችን ላይ ድርጅቱ ያዘጋጃቸውን ቪዲዮዎችና ሌሎች የማስተማሪያ መሣሪያዎች መጠቀም ያለብን ለምንድን ነው?