በቀጥታ ወደ ዋናው ጉዳይ ግባ

በቀጥታ ወደ ርዕስ ማውጫው ሂድ

ክርስቲያናዊ ሕይወት

ተግሣጽ የይሖዋ የፍቅር መግለጫ ነው

ተግሣጽ የይሖዋ የፍቅር መግለጫ ነው

ተግሣጽ በአብዛኛው መመሪያና ትምህርት ከመስጠት ጋር ይያያዛል፤ ሆኖም እርማትንና ወቀሳን ሊያካትትም ይችላል። ይሖዋ ተግሣጽ የሚሰጠን እሱን ተቀባይነት ባለው መንገድ እንድናመልከው ሲል ነው። (ሮም 12:1፤ ዕብ 12:10, 11) አንዳንድ ጊዜ ተግሣጽ ሊያምም ይችላል፤ ሆኖም ጽድቅና በረከት ያስገኝልናል። (ምሳሌ 10:7) ታዲያ ተግሣጽ የሚሰጡም ሆነ የሚቀበሉ ሰዎች ምን ማስታወስ ይኖርባቸዋል?

ሰጪው። ሽማግሌዎች፣ ወላጆችም ሆኑ ሌሎች ተግሣጽ የሚሰጡት እንደ ይሖዋ በደግነትና በፍቅር ሊሆን ይገባል። (ኤር 46:28) ጠንከር ያለ ተግሣጽም ቢሆን ለሁኔታው የሚመጥን መሆን አለበት፤ ተግሣጹን የሚሰጡ ሰዎችም እንዲህ እንዲያደርጉ የሚያነሳሳቸው ፍቅር ሊሆን ይገባል።—ቲቶ 1:13

ተቀባዩ። ተግሣጽ የሚሰጠን በምንም መልክ ቢሆን ተግሣጹን ለመቀበል እንቢተኞች መሆን የለብንም፤ ከዚህ ይልቅ ተግሣጹን ተቀብለን በሥራ ላይ ለማዋል ፈጣኖች መሆን አለብን። (ምሳሌ 3:11, 12) ሁላችንም ፍጹማን ባለመሆናችን ተግሣጽ ያስፈልገናል፤ ተግሣጹ የሚመጣው በተለያየ መልክ ሊሆን ይችላል። መጽሐፍ ቅዱስ ላይ ከምናነበው ወይም በጉባኤ ስብሰባዎች ላይ ከምንሰማው ነገር ተግሣጽ ልናገኝ እንችላለን። ወይም ደግሞ አንዳንዶች በፍርድ ኮሚቴ ተግሣጽ ሊሰጣቸው ይችላል። ተግሣጽን መቀበል የኋላ ኋላ ሕይወት ያስገኛል።—ምሳሌ 10:17

“ይሖዋ የሚወዳቸውን ይገሥጻል” የሚለውን ቪዲዮ ተመልከት፤ ከዚያም የሚከተሉትን ጥያቄዎች ለመመለስ ሞክር፦

  • የካነን የልጅነት ሕይወት ምን ይመስል ነበር? በኋላ የተቀየረውስ እንዴት ነው?

  • ይሖዋ ምን ፍቅራዊ ተግሣጽ ሰጥቶታል?

  • ይሖዋ የሚሰጥህን ተግሣጽ በደስታ ተቀበል

    እሱ ካጋጠመው ነገር ምን እንማራለን?