በቀጥታ ወደ ዋናው ጉዳይ ግባ

በቀጥታ ወደ ርዕስ ማውጫው ሂድ

ክርስቲያናዊ ሕይወት

“በመጨረሻዎቹ ቀናት” መጨረሻ ለሚያጋጥሙ ነገሮች ዝግጁ ሁኑ

“በመጨረሻዎቹ ቀናት” መጨረሻ ለሚያጋጥሙ ነገሮች ዝግጁ ሁኑ

የምንኖረው “በመጨረሻዎቹ ቀናት” መጨረሻ እንደመሆኑ መጠን የሚያጋጥሙን ችግሮች እየተባባሱ እንደሚሄዱ እንጠብቃለን። (2ጢሞ 3:1፤ ማቴ 24:8) አደጋ በሚከሰትበት ወቅት የይሖዋ ሕዝቦች ብዙውን ጊዜ ወቅታዊና ሕይወት አድን መመሪያ ይሰጣቸዋል። በዚያ ጊዜ በሕይወት መትረፋችን የተመካው የሚሰጠንን መመሪያ በመታዘዝ ከአሁኑ ዝግጁ በመሆናችን ላይ ነው፤ በመንፈሳዊም ሆነ በቁሳዊ ዝግጁ መሆን አለብን።—ሉቃስ 16:10

  • በመንፈሳዊ ዝግጁ መሆን፦ ጥሩ መንፈሳዊ ልማድ አዳብሩ። በተለያዩ የአገልግሎት ዘርፎች መካፈልን ተለማመዱ። በጉባኤያችሁ ካሉ አስፋፊዎች ጋር ለተወሰነ ጊዜ መገናኘት ባትችሉ አትደናገጡ። (ኢሳ 30:15) መቼም ቢሆን ከይሖዋና ከኢየሱስ ልትለዩ እንደማትችሉ አስታውሱ።—od 176 አን. 15-17

  • በቁሳዊ ዝግጁ መሆን፦ ለአደጋ ጊዜ የሚሆን ቦርሳ አዘጋጁ፤ ከዚህም በተጨማሪ ረዘም ላለ ጊዜ በአንድ ቦታ ተጠልላችሁ ለመኖር ብትገደዱ ለዚያ የሚያስፈልጋችሁን ምግብ፣ ውኃ፣ መድኃኒትና ሌሎች መሰል ነገሮችን ምክንያታዊ በሆነ መጠን አስቀምጡ።—ምሳሌ 22:3g17.5 4, 6

የተፈጥሮ አደጋ ቢያጋጥም ዝግጁ ናችሁ? የሚለውን ቪዲዮ ተመልከት፤ ከዚያም የሚከተሉትን ጥያቄዎች ለመመለስ ሞክር፦

  • ለአደጋ ጊዜ ራሳችንን በመንፈሳዊ ማዘጋጀት የምንችለው እንዴት ነው?

  • የሚከተሉትን ነገሮች ማድረጋችን አስፈላጊ የሆነው ለምንድን ነው?

    • ከሽማግሌዎች ጋር ጥሩ የሐሳብ ልውውጥ ማድረግ

    • ለአደጋ ጊዜ የሚሆን ቦርሳ ማዘጋጀት

    • ምን ዓይነት አደጋዎች ሊከሰቱ እንደሚችሉና በእያንዳንዱ ሁኔታ ሥር ምን ማድረግ እንዳለብን መወያየት

  • አደጋ ያጋጠማቸውን መርዳት የምንችልባቸው ሦስት መንገዶች የትኞቹ ናቸው?

ራስህን እንዲህ እያልክ ጠይቅ፦ ‘ለአደጋ ዝግጁ መሆንን በተመለከተ ከኮቪድ-19 ወረርሽኝ ምን ትምህርት አግኝቻለሁ?’