በቀጥታ ወደ ዋናው ጉዳይ ግባ

በቀጥታ ወደ ርዕስ ማውጫው ሂድ

ክርስቲያናዊ ሕይወት

ምኞታችሁን ተቆጣጠሩት

ምኞታችሁን ተቆጣጠሩት

ፍጹማን ያልሆንን ሰዎች እንደመሆናችን መጠን ምኞታችንን ለመቆጣጠር ያለማቋረጥ መታገል ይጠበቅብናል። ምኞታችንን ካልተቆጣጠርነው የይሖዋን ሞገስ ሊያሳጣን ይችላል። ለምሳሌ አንዳንዶች ምግብ፣ ልብስ እና መጠለያ ለማግኘት ያላቸው ምኞት ለአምላክ ካላቸው ፍቅር ሊበልጥባቸው ይችላል። ሌሎች ሰዎች ፆታዊ ምኞታቸውን ለማርካት ሲሉ የአምላክን መሥፈርቶች ይጥሳሉ። (ሮም 1:26, 27) ሌሎች ደግሞ ለመወደድ ወይም ተቀባይነት ለማግኘት ካላቸው ምኞት የተነሳ ለእኩዮች ተጽዕኖ እጅ ይሰጣሉ።—ዘፀ 23:2

ምኞታችንን መቆጣጠር የምንችለው እንዴት ነው? በመንፈሳዊ ነገሮች ላይ ለማተኮር አቅማችን የፈቀደውን ሁሉ ማድረግ ይኖርብናል። (ማቴ 4:4) በተጨማሪም ይሖዋ ምኞታችንን ለመቆጣጠር እንዲረዳን ልንለምነው ይገባል። ለምን? ምክንያቱም ለእኛ ከሁሉ የተሻለውን የሚያውቀው እሱ ነው፤ እንዲሁም ተገቢ የሆኑ ፍላጎቶቻችንን እንዴት እንደሚያረካልን ያውቃል።—መዝ 145:16

ስታጨስ እንዳትጨስ የሚለውን ቪዲዮ ተመልከት፤ ከዚያም የሚከተሉትን ጥያቄዎች ለመመለስ ሞክር፦

  • አንዳንዶች የሚያጨሱት ለምንድን ነው?

  • ማጨስ ምን ጉዳት ያስከትላል?

  • ትንባሆም ሆነ ኤሌክትሮኒክ ሲጋራ ማጨስ ስህተት የሆነው ለምንድን ነው?—2ቆሮ 7:1

  • የማጨስ ፍላጎትን ማሸነፍ ትችላለህ!

    ለማጨስ ስትፈተን ‘እንቢ’ ማለት ወይም ማጨስህን ማቆም የምትችለው እንዴት ነው?