በቀጥታ ወደ ዋናው ጉዳይ ግባ

በቀጥታ ወደ ርዕስ ማውጫው ሂድ

ክርስቲያናዊ ሕይወት

ለዘላለም በደስታ ኑር! የተባለውን መጽሐፍ ተጠቅማችሁ ሌሎች በይሖዋ እና በኢየሱስ ላይ እምነት እንዲገነቡ እርዱ

ለዘላለም በደስታ ኑር! የተባለውን መጽሐፍ ተጠቅማችሁ ሌሎች በይሖዋ እና በኢየሱስ ላይ እምነት እንዲገነቡ እርዱ

የመጽሐፍ ቅዱስ ጥናቶች አምላክን ማስደሰት እንዲችሉ ጠንካራ እምነት ማዳበር አለባቸው። (ዕብ 11:6) ለዘላለም በደስታ ኑር! የተባለውን መጽሐፍ በመጠቀም ልባቸውን መንካት እንችላለን። ይህ የማስጠኛ መጽሐፍ ቁልፍ ጥቅሶችን፣ ግልጽ የሆኑ ማብራሪያዎችን፣ ውጤታማ ጥያቄዎችን፣ ቀልብ የሚስቡ ቪዲዮዎችንና ውብ ሥዕሎችን የያዘ ነው። ጥናቶቻችን ክርስቲያናዊ ባሕርያት እንዲያዳብሩና ከአምላክ ጋር ወዳጅነት እንዲመሠርቱ በመርዳት እሳትን መቋቋም በሚችሉ ቁሳቁሶች መገንባት እንችላለን።—1ቆሮ 3:12-15

አንዳንድ ሰዎች ከማያዩት አምላክ ጋር ወዳጅነት መመሥረት የሚቻል ነገር እንደሆነ አይሰማቸውም። በመሆኑም ይሖዋን እንዲያውቁትና እንዲታመኑበት ልንረዳቸው ይገባል።

“ለዘላለም በደስታ ኑር!” የተባለውን መጽሐፍ ተጠቅማችሁ ሌሎች በይሖዋ ላይ እምነት እንዲገነቡ እርዱ የሚለውን ቪዲዮ ተመልከት፤ ከዚያም የሚከተሉትን ጥያቄዎች ለመመለስ ሞክር፦

  • አስጠኚዋ ለጥናቱ በደንብ እንደተዘጋጀች እንዴት እናውቃለን?

  • ከኢሳይያስ 41:10, 13 ጋር በተያያዘ ተማሪዋ ስሜቷን እንድትገልጽ ለመርዳት በሚገባ የታሰበባቸው ተጨማሪ ጥያቄዎች የተጠቀመችው እንዴት ነው?

  • ቪዲዮውና የመጽሐፍ ቅዱስ ጥቅሶቹ በተማሪዋ ላይ ምን ውጤት አምጥተዋል?

ብዙ ሰዎች የቤዛው ዝግጅት በደንብ አይገባቸውም፤ ወይም ደግሞ ቤዛው አምላክ በግለሰብ ደረጃ የሰጣቸው ስጦታ እንደሆነ አይሰማቸውም። (ገላ 2:20) ስለዚህ በኢየሱስ ቤዛዊ መሥዋዕት ላይ እምነት እንዲያዳብሩ ልንረዳቸው ይገባል።

“ለዘላለም በደስታ ኑር!” የተባለውን መጽሐፍ ተጠቅማችሁ ሌሎች በኢየሱስ ላይ እምነት እንዲገነቡ እርዱ የሚለውን ቪዲዮ ተመልከት፤ ከዚያም የሚከተሉትን ጥያቄዎች ለመመለስ ሞክር፦

  • አስጠኚው ለጥናቱ በደንብ እንደተዘጋጀ እንዴት እናውቃለን?

  • “ምርምር አድርግ” በሚለው ክፍል ውስጥ ያለውን ነጥብ ተማሪውን ለመርዳት የተጠቀመበት እንዴት ነው?

  • ጸሎት ለተማሪው ወሳኝ የሆነው ለምንድን ነው?