በቀጥታ ወደ ዋናው ጉዳይ ግባ

በቀጥታ ወደ ርዕስ ማውጫው ሂድ

ክርስቲያናዊ ሕይወት

“ፍቅር . . . አይታበይም”

“ፍቅር . . . አይታበይም”

ፍቅር ትሕትና እንድናሳይ ይረዳናል። (1ቆሮ 13:4) ለወንድሞቻችን ፍቅር ካለን ራሳችንን ከእነሱ ከፍ አድርገን አንመለከትም። የሌሎችን መልካም ጎን እናያለን፤ እንዲሁም ችሎታችንን እነሱን ለመርዳት እንጠቀምበታለን። (ፊልጵ 2:3, 4) እንዲህ ያለውን ፍቅር ይበልጥ ባሳየን መጠን ይሖዋም ፈቃዱን ለማድረግ ይበልጥ ይጠቀምብናል።

ፍቅር የሚያደርጋቸውና የማያደርጋቸው ነገሮች—አይታበይም የሚለውን ቪዲዮ ተመልከት፤ ከዚያም የሚከተሉትን ጥያቄዎች ለመመለስ ሞክር፦

  • አቢሴሎም የትኞቹ ስጦታዎች ነበሩት?

  • ስጦታውን ያለአግባብ የተጠቀመበት እንዴት ነው?

  • እንዳንታበይ ምን ይረዳናል?—ገላ 5:26