በቀጥታ ወደ ዋናው ጉዳይ ግባ

በቀጥታ ወደ ርዕስ ማውጫው ሂድ

ክርስቲያናዊ ሕይወት

“ፍቅር . . . ሁሉን ተስፋ ያደርጋል”

“ፍቅር . . . ሁሉን ተስፋ ያደርጋል”

ከራስ ወዳድነት ነፃ የሆነ ፍቅር ወንድሞቻችን ጥሩ ውሳኔ እንደሚያደርጉ ተስፋ እንድናደርግ ያነሳሳናል። (1ቆሮ 13:4, 7) ለምሳሌ አንድ ወንድም ኃጢአት ሠርቶ ተግሣጽ ቢሰጠው እሱን ለመርዳት ለሚደረገው ጥረት በጎ ምላሽ እንደሚሰጥ ተስፋ እናደርጋለን። ደካማ እምነት ያላቸውን ሰዎች በትዕግሥት እንይዛቸዋለን፤ እንዲሁም እነሱን ለመርዳት ጥረት እናደርጋለን። (ሮም 15:1) አንድ ሰው ጉባኤውን ቢተው ደግሞ አንድ ቀን እንደሚመለስ ተስፋ እናደርጋለን።—ሉቃስ 15:17, 18

ፍቅር የሚያደርጋቸውና የማያደርጋቸው ነገሮች—ሁሉን ተስፋ ያደርጋል የሚለውን ቪዲዮ ተመልከት፤ ከዚያም የሚከተሉትን ጥያቄዎች ለመመለስ ሞክር፦

  • አበኔር ምን ዓይነት ለውጥ አደረገ?

  • ዳዊት ለአበኔር ጥያቄ ምን ምላሽ ሰጠ? ኢዮዓብስ?

  • ወንድሞቻችን ጥሩ ውሳኔ እንደሚያደርጉ ተስፋ ማድረግ ያለብን ለምንድን ነው?