በቀጥታ ወደ ዋናው ጉዳይ ግባ

በቀጥታ ወደ ርዕስ ማውጫው ሂድ

ክርስቲያናዊ ሕይወት

“ፍቅር በዓመፅ አይደሰትም”

“ፍቅር በዓመፅ አይደሰትም”

እውነተኛ ክርስቲያኖች በሁሉም የሕይወታቸው ዘርፎች ፍቅር ለማሳየት ጥረት ያደርጋሉ። “ፍቅር በዓመፅ አይደሰትም።” (1ቆሮ 13:4, 6) በመሆኑም እንደ ፆታ ብልግና እና ዓመፅ ያሉትን ነገሮች ከሚያበረታቱ መዝናኛዎች እንርቃለን። በተጨማሪም ጉዳት ያደረሱብንን ሰዎች ጨምሮ በሌሎች ላይ መጥፎ ነገር ሲደርስ አንደሰትም።—ምሳሌ 17:5

ፍቅር የሚያደርጋቸውና የማያደርጋቸው ነገሮች—በዓመፅ አይደሰትም የሚለውን ቪዲዮ ተመልከት፤ ከዚያም የሚከተሉትን ጥያቄዎች ለመመለስ ሞክር፦

  • ዳዊት ሳኦልና ዮናታን እንደሞቱ ሲነገረው ምን ተሰማው?

  • ዳዊት ለሳኦልና ለዮናታን የትኛውን ሙሾ አቀናበረ?

  • ዳዊት በሳኦል ሞት ያልተደሰተው ለምንድን ነው?