በቀጥታ ወደ ዋናው ጉዳይ ግባ

በቀጥታ ወደ ርዕስ ማውጫው ሂድ

ክርስቲያናዊ ሕይወት

ሕዝባዊ ዓመፅ ቢያጋጥም ዝግጁ ናችሁ?

ሕዝባዊ ዓመፅ ቢያጋጥም ዝግጁ ናችሁ?

የዚህ ሥርዓት መጨረሻ እየቀረበ በሄደ መጠን ሕዝባዊ ዓመፅ፣ ሽብርተኝነትና ጦርነት እየበዙ እንደሚሄዱ እንጠብቃለን። (ራእይ 6:4) እንዲህ ላለው ሁኔታ ከአሁኑ መዘጋጀት የምንችለው እንዴት ነው?

  • በመንፈሳዊ ዝግጁ መሆን፦ በይሖዋ እና በድርጅቱ ላይ ያላችሁን እምነት ለማጠናከር እንዲሁም ገለልተኝነታችሁን ለመጠበቅ የሚረዱ የመጽሐፍ ቅዱስ መሠረታዊ ሥርዓቶችንና ዘገባዎችን ለማግኘት ሞክሩ። (ምሳሌ 12:5jr-E 125-126 አን. 23-24) በጉባኤው ውስጥ ካሉ ወንድሞችና እህቶች ጋር ጠንካራ ወዳጅነት ለመመሥረት ጊዜው አሁን ነው።—1ጴጥ 4:7, 8

  • በቁሳዊ ዝግጁ መሆን፦ በቤታችሁ ለመሸሸግ ብትገደዱ ምን እንደምታደርጉ አስቀድማችሁ ተዘጋጁ፤ እንዲሁም የሚያስፈልጓችሁን ቁሳቁሶች ሚዛናዊ በሆነ መጠን አከማቹ። በተጨማሪም ቤታችሁን ለቃችሁ ለመሄድ ከተገደዳችሁ ምን እንደምታደርጉ አቅዱ። ለአደጋ ጊዜ ባዘጋጃችሁት ቦርሳ ወይም ሻንጣ ውስጥ ምን እንዳለ አጣሩ፤ እንደ ማስክ እና ጓንት ያሉ የመከላከያ ቁሳቁሶች እንዲሁም ገንዘብ ቦርሳው ውስጥ ያዙ። ሽማግሌዎችን ማግኘት የምትችሉበትን መንገድ እወቁ፤ እነሱም እናንተን ማግኘት የሚችሉ መሆኑን አረጋግጡ።—ኢሳ 32:2g17.5 3-7

በዓመፁ ወቅት መንፈሳዊ ልማዳችሁን አታቋርጡ። (ፊልጵ 1:10) መኖሪያችሁን ለቃችሁ ለመሄድ ካልተገደዳችሁ በቀር ከቦታ ቦታ አትንቀሳቀሱ። (ማቴ 10:16) ያላችሁን ምግብና ሌሎች ቁሳቁሶች ለሌሎች አካፍሉ።—ሮም 12:13

አደጋ ቢያጋጥም ዝግጁ ናችሁ? የሚለውን ቪዲዮ ተመልከት፤ ከዚያም የሚከተሉትን ጥያቄዎች ለመመለስ ሞክር፦

  • በአደጋ ወቅት ይሖዋ የሚረዳን እንዴት ነው?

  • ዝግጁ ለመሆን የትኞቹን እርምጃዎች መውሰድ እንችላለን?

  • አደጋ የደረሰባቸውን መርዳት የምንችለው እንዴት ነው?