በቀጥታ ወደ ዋናው ጉዳይ ግባ

በቀጥታ ወደ ርዕስ ማውጫው ሂድ

ክርስቲያናዊ ሕይወት

በአገልግሎታችሁ ላይ ወቅታዊ ጉዳዮችን ተጠቀሙ

በአገልግሎታችሁ ላይ ወቅታዊ ጉዳዮችን ተጠቀሙ

ኢየሱስ በአገልግሎቱ ላይ ሰዎችን ለማስተማር ወቅታዊ ጉዳዮችን ተጠቅሟል። (ሉቃስ 13:1-5) እናንተም ሰዎች የመንግሥቱን መልእክት ለመስማት እንዲጓጉ ለማድረግ ወቅታዊ ጉዳዮችን መጠቀም ትችላላችሁ። ስለ ኑሮ ውድነት፣ የተፈጥሮ አደጋ፣ ሕዝባዊ ዓመፅ፣ የዕፅ ሱሰኝነት ወይም ሌላ ጉዳይ ከጠቀሳችሁ በኋላ ግለሰቡ ቆም ብሎ እንዲያስብ የሚያደርግ ጥያቄ አንሱ። እንዲህ ብላችሁ ልትጠይቁት ትችላላችሁ፦ “. . . የማይኖርበት ጊዜ የሚመጣ ይመስልሃል?” ወይም “ለ. . . መፍትሔው ምን ይመስልሃል?” ከዚያም ከርዕሰ ጉዳዩ ጋር የሚያያዝ የመጽሐፍ ቅዱስ ጥቅስ አንብቡ። ግለሰቡ ፍላጎት ካሳየ ከማስተማሪያ መሣሪያዎቻችን መካከል አንድ ቪዲዮ ወይም ጽሑፍ አሳዩት። በክልላችን ውስጥ ያሉትን ሰዎች ልብ ለመንካት ስንጥር ‘ለምሥራቹ ስንል ሁሉን ነገር እናድርግ።’—1ቆሮ 9:22, 23

በክልላችሁ ውስጥ ያሉትን ሰዎች ትኩረት የሚስቡት ርዕሰ ጉዳዮች የትኞቹ ናቸው?