በቀጥታ ወደ ዋናው ጉዳይ ግባ

በቀጥታ ወደ ርዕስ ማውጫው ሂድ

ክርስቲያናዊ ሕይወት

ራሳችሁን ከክህደት ጠብቁ

ራሳችሁን ከክህደት ጠብቁ

ሰይጣንና በእሱ ቁጥጥር ሥር ያሉ ሰዎች እምነታችንን ለማዳከም ሲሉ እውነትን ከውሸት ጋር ቀላቅለው ያቀርባሉ። (2ቆሮ 11:3) ለምሳሌ አሦራውያን የይሖዋን ሕዝቦች ተስፋ ለማስቆረጥ ሲሉ በከፊል እውነት የሆኑ ሐሳቦችንና ዓይን ያወጡ ውሸቶችን ተናግረው ነበር። (2ዜና 32:10-15) በዛሬው ጊዜ ያሉ ከሃዲዎችም ተመሳሳይ ዘዴዎችን ይጠቀማሉ። ታዲያ ከሃዲዎች ለሚያስፋፏቸው ትምህርቶች ምን አመለካከት ሊኖረን ይገባል? እንደ መርዝ ልንሸሻቸው ይገባል! ልናነባቸው፣ ምላሽ ልንሰጥባቸው ወይም ለሌላ ሰው ልናነሳቸው ፈጽሞ አይገባም። በይሖዋና በድርጅቱ ላይ ጥርጣሬ እንዲያድርብን ለማድረግ ታስበው የተዘጋጁ መረጃዎችን ቶሎ ለይተን ማወቅና እንዲህ ካለው መረጃ መራቅ ይኖርብናል።—ይሁዳ 3, 4

‘ለእምነት ብርቱ ተጋድሎ አድርጉ’!—ተቀንጭቦ የተወሰደ የሚለውን ቪዲዮ ተመልከት፤ ከዚያም የሚከተሉትን ጥያቄዎች ለመመለስ ሞክር፦

  • የኢንተርኔት ፎረሞችን የምንጠቀም ከሆነ ጠንቃቃ መሆን ያለብን ለምንድን ነው?

  • በሮም 16:17 ላይ የሚገኘውን ምክር መከተል የምንችለው እንዴት ነው?