ክርስቲያናዊ ሕይወት
በድምፅ የተዘጋጀውን መጽሐፍ ቅዱስ በሚገባ እየተጠቀማችሁበት ነው?
በድምፅ የተዘጋጀው መጽሐፍ ቅዱስ ምንድን ነው? ተሻሽሎ የተዘጋጀው አዲስ ዓለም ትርጉም በድምፅ ተቀርጾ በተቻለ መጠን በብዙ ቋንቋዎች መጽሐፍ በመጽሐፍ እየወጣ ነው። በድምፅ የተዘጋጀው መጽሐፍ ቅዱስ ካሉት ለየት ያሉ ገጽታዎች አንዱ ለእያንዳንዱ የመጽሐፍ ቅዱስ ባለታሪክ የተለያየ ድምፅ መጠቀሙ ነው። ቃላቱ የሚነበቡት ተገቢው አጽንዖትና ስሜት ተሰጥቷቸው ነው፤ ይህም የመጽሐፍ ቅዱስን መልእክት በትክክል ለማስተላለፍ ያስችላል።
አንዳንዶች በድምፅ ከተዘጋጀው መጽሐፍ ቅዱስ ምን ጥቅም እያገኙ ነው? በድምፅ የተዘጋጀውን መጽሐፍ ቅዱስ አዘውትረው የሚያዳምጡ ብዙ ሰዎች የአምላክ ቃል ሕያው እንዲሆንላቸው እንደረዳቸው ይናገራሉ። ለእያንዳንዱ የመጽሐፍ ቅዱስ ባለታሪክ የተለያየ አንባቢ መኖሩ ክንውኖቹን በዓይነ ሕሊናቸው ለመሣልና ሐሳቡን በግልጽ ለመረዳት እንደሚያግዛቸው ገልጸዋል። (ምሳሌ 4:5) በተጨማሪም ብዙዎች በድምፅ የተዘጋጀውን መጽሐፍ ቅዱስ ማዳመጣቸው በጭንቀት በሚዋጡበት ጊዜ ለመረጋጋት እንደሚረዳቸው አስተውለዋል።—መዝ 94:19
የአምላክ ቃል ጮክ ተብሎ ሲነበብ መስማታችን ለሥራ ሊያነሳሳን ይችላል። (2ዜና 34:19-21) በድምፅ የተዘጋጀው መጽሐፍ ቅዱስ መረዳት በምትችሉት ቋንቋ በሙሉ ወይም በከፊል የሚገኝ ከሆነ አዘውትራችሁ የማዳመጥ ልማድ ማዳበር ትችሉ ይሆን?
መጽሐፍ ቅዱስን በድምፅ ማዘጋጀት—ተቀንጭቦ የተወሰደ የሚለውን ቪዲዮ ተመልከት፤ ከዚያም የሚከተለውን ጥያቄ ለመመለስ ሞክር፦
መጽሐፍ ቅዱስ በድምፅ ከተዘጋጀበት መንገድ ትኩረታችሁን የሳበው ምንድን ነው?