በቀጥታ ወደ ዋናው ጉዳይ ግባ

በቀጥታ ወደ ርዕስ ማውጫው ሂድ

ክርስቲያናዊ ሕይወት

ውይይት በመጀመር ደስታ ማግኘት

ውይይት በመጀመር ደስታ ማግኘት

ምሥክርነት መስጠት ከሚቻልባቸው አስደሳችና ውጤታማ መንገዶች አንዱ መደበኛ ያልሆነ ጭውውት መጀመር ነው። ይሁንና ወደ መጽሐፍ ቅዱሳዊ ርዕሰ ጉዳይ መግባት ስለምንችልበት መንገድ ከልክ በላይ ካሰብን ጭውውት መጀመር ሊያስፈራን ይችላል። ምሥክርነት መስጠት ስለምትችሉበት መንገድ ከልክ በላይ ከመጨነቅ ይልቅ ለሰዎቹ አሳቢነት በማሳየት ላይ ትኩረት አድርጉ። (ማቴ 22:39፤ ፊልጵ 2:4) በጭውውቱ ወቅት ስለ እምነታችሁ መናገር የምትችሉበት አጋጣሚ ካገኛችሁ ደግሞ ሊረዷችሁ የሚችሉ በርካታ መሣሪያዎች አሉ።

የሚከተሉት መሣሪያዎች በጭውውቱ ወቅት በተነሳው ርዕሰ ጉዳይ ላይ ተመሥርታችሁ ምሥክርነት ለመስጠት የሚረዷችሁ እንዴት ነው?

‘ብረት ብረትን ይስላል’—ውይይት መጀመር የሚለውን ቪዲዮ ተመልከት፤ ከዚያም የሚከተለውን ጥያቄ ለመመለስ ሞክር፦

ውይይት የመጀመር ችሎታችንን ለማሻሻል የሚረዱን ሦስት እርምጃዎች የትኞቹ ናቸው?