በቀጥታ ወደ ዋናው ጉዳይ ግባ

በቀጥታ ወደ ርዕስ ማውጫው ሂድ

ክርስቲያናዊ ሕይወት

ለራሳችሁ የይሖዋ ዓይነት አመለካከት ይኑራችሁ

ለራሳችሁ የይሖዋ ዓይነት አመለካከት ይኑራችሁ

“ይሖዋ በሕዝቡ ደስ ይሰኛል።” (መዝ 149:4) ፍጹማን ባንሆንም እንኳ መልካም ባሕርያችንን እና ችሎታችንን ይመለከታል። ይሁንና አንዳንድ ጊዜ ለራሳችን እንዲህ ያለ ሚዛናዊ አመለካከት መያዝ ሊከብደን ይችላል። ሰዎች እኛን የሚይዙበት መንገድ ለራሳችን ዝቅተኛ አመለካከት እንዲኖረን ሊያደርግ ይችላል። ወይም ደግሞ ቀደም ሲል በሠራናቸው ስህተቶች የተነሳ ይሖዋ በእርግጥ የሚወደን መሆኑን ልንጠራጠር እንችላለን። እንዲህ ዓይነት ስሜት ሲሰማን ምን ሊረዳን ይችላል?

ይሖዋ የሚያየው ሰው በሚያይበት መንገድ እንዳልሆነ አስታውሱ። (1ሳሙ 16:7) ይህም ሲባል ይሖዋ የሚያየን እኛ ራሳችንን በምናይበት መንገድ አይደለም ማለት ነው። ደስ የሚለው፣ መጽሐፍ ቅዱስ ይሖዋ ለእኛ ያለውን አመለካከት እንድናስተውል ይረዳናል። ይሖዋ አገልጋዮቹን ምን ያህል እንደሚወዳቸው የሚያሳዩ የመጽሐፍ ቅዱስ ጥቅሶችንና ዘገባዎችን በመመርመር የይሖዋን አመለካከት መረዳት እንችላለን።

ልባችሁ በይሖዋ ፊት እንዲረጋጋ አድርጉ የሚለውን ቪዲዮ ተመልከት፤ ከዚያም የሚከተሉትን ጥያቄዎች ለመመለስ ሞክር፦

  • ስለ አንድ ሯጭና ስለ አባቱ ከሚገልጸው ምሳሌ ይሖዋ ለእኛ ስላለው አመለካከት ምን እንማራለን?

  • ከባድ ኃጢአት የፈጸመ ሰው ከይሖዋ ጋር ያለውን ዝምድና ለማደስ አስፈላጊውን እርምጃ ከወሰደ ልቡ በይሖዋ ፊት እንዲረጋጋ ማድረግ የሚችለው እንዴት ነው?—1ዮሐ 3:19, 20

  • ወንድም ስለ ዳዊትና ስለ ኢዮሳፍጥ የሚገልጹትን ዘገባዎች ማንበቡና በዚያ ላይ ማሰላሰሉ የጠቀመው እንዴት ነው?