በቀጥታ ወደ ዋናው ጉዳይ ግባ

በቀጥታ ወደ ርዕስ ማውጫው ሂድ

ክርስቲያናዊ ሕይወት

ይሖዋ “አባት ለሌላቸው ልጆች አባት” ነው

ይሖዋ “አባት ለሌላቸው ልጆች አባት” ነው

በየዓመቱ በርካታ ወጣቶች የይሖዋ ወዳጅ ለመሆን ውሳኔ ያደርጋሉ። (መዝ 110:3) ይሖዋ ስለ እያንዳንዳችሁ በጥልቅ ያስባል። የሚያጋጥሟችሁን ችግሮች ይረዳል፤ እንዲሁም እሱን እንድታገለግሉ እንደሚረዳችሁ ቃል ገብቶላችኋል። ነጠላ ወላጅ የሚያሳድጋችሁ ልጆች ከሆናችሁ ይሖዋ “አባት ለሌላቸው ልጆች አባት” እንደሚሆን አስታውሱ። (መዝ 68:5) የቤተሰባችሁ ሁኔታ ምንም ይሁን ምን ይሖዋ በሚሰጣችሁ ሥልጠና ስኬታማ መሆን ትችላላችሁ።—1ጴጥ 5:10

ለእምነት ብርቱ ትግል በማድረግ የተሳካላቸው—በነጠላ ወላጅ የሚያድጉ ልጆች የሚለውን ቪዲዮ ተመልከት፤ ከዚያም የሚከተሉትን ጥያቄዎች ለመመለስ ሞክር፦

  • ከታሚ፣ ከቻርልስና ከጂሚ ምሳሌ ምን ትምህርት አግኝታችኋል?

  • መዝሙር 27:10 በነጠላ ወላጅ ለሚያድጉ ልጆች ምን ዋስትና ይሰጣል?