ክርስቲያናዊ ሕይወት
ለኢኮኖሚ ቀውስ ተዘጋጅታችኋል?
በዓለም ዙሪያ የኢኮኖሚ አለመረጋጋት ቢከሰት አንደናገጥም። ለምን? ምክንያቱም የምንኖረው በመጨረሻዎቹ ቀናት መጨረሻ እንደሆነ እናውቃለን፤ መጽሐፍ ቅዱስም ተስፋችንን “አስተማማኝነት በሌለው ሀብት” ላይ እንዳንጥል ይመክረናል። (1ጢሞ 6:17፤ 2ጢሞ 3:1) ለኢኮኖሚ ቀውስ መዘጋጀት የምንችልበትን መንገድ በተመለከተ ከኢዮሳፍጥ ምሳሌ ምን እንማራለን?
የጠላት ሠራዊት ይሁዳን ለመውረር በመጣበት ወቅት ኢዮሳፍጥ በይሖዋ ታምኗል። (2ዜና 20:9-12) በተጨማሪም ምሽጎችን በመገንባትና የጦር ሰፈሮችን በማቋቋም ብሔሩን ለሚሰነዘርባቸው ጥቃት ለማዘጋጀት ተግባራዊ እርምጃ ወስዷል። (2ዜና 17:1, 2, 12, 13) እኛም የሚያጋጥመንን አስቸጋሪ ሁኔታ ለመቋቋም እንደ ኢዮሳፍጥ በይሖዋ መታመንና ተግባራዊ እርምጃ መውሰድ ይኖርብናል።
አደጋ ቢያጋጥም ዝግጁ ናችሁ? የሚለውን ቪዲዮ ተመልከት፤ ከዚያም የሚከተሉትን ጥያቄዎች ለመመለስ ሞክር፦
-
ለአደጋ ለመዘጋጀት በግለሰብ ደረጃ ምን ማድረግ እንችላለን?
-
ሌሎችን ለመርዳት መዘጋጀት የምንችለው እንዴት ነው?