በቀጥታ ወደ ዋናው ጉዳይ ግባ

በቀጥታ ወደ ርዕስ ማውጫው ሂድ

ከሰኔ 3-9

መዝሙር 45–47

ከሰኔ 3-9

መዝሙር 27 እና ጸሎት | የመግቢያ ሐሳብ (1 ደቂቃ)

ከአምላክ ቃል የሚገኝ ውድ ሀብት

ኢየሱስ ክርስቶስ ከሙሽራይቱ ማለትም ከ144,000ዎቹ ጋር ሆኖ

1. ስለ ንጉሡ ሠርግ የሚገልጽ መዝሙር

(10 ደቂቃ)

መዝሙር 45 ስለ መሲሐዊው ንጉሥ ሠርግ ይናገራል (መዝ 45:1, 13, 14w14 2/15 9-10 አን. 8-9)

የንጉሡ ሠርግ የሚካሄደው ከአርማጌዶን በኋላ ነው (መዝ 45:3, 4w22.05 17 አን. 10-12፤ የሽፋኑን ሥዕል ተመልከት)

ይህ ሠርግ ለሰው ልጆች በሙሉ በረከት ያስገኛል (መዝ 46:8-11it-2 1169)


ራስህን እንዲህ ብለህ ጠይቅ፦ ‘ስለ ንጉሣችን ስለ ኢየሱስ ክርስቶስ የሚገልጸውን ምሥራች ለማወጅ ልቤ “ተነሳስቷል?”’—መዝ 45:1

2. መንፈሳዊ ዕንቁዎች

(10 ደቂቃ)

  • መዝ 45:16—ይህ ጥቅስ በገነት ውስጥ ስለሚኖረው ሕይወት ምን ያስተምረናል? (w17.04 11 አን. 9)

  • ከዚህ ሳምንት የመጽሐፍ ቅዱስ ንባብ ምን መንፈሳዊ ዕንቁዎች አግኝታችኋል?

3. የመጽሐፍ ቅዱስ ንባብ

(4 ደቂቃ) መዝ 45:1-17 (th ጥናት 5)

በአገልግሎት ውጤታማ ለመሆን ተጣጣር

4. ውይይት መጀመር

(3 ደቂቃ) መደበኛ ያልሆነ ምሥክርነት። (lmd ምዕራፍ 1 ነጥብ 3)

5. ንግግር

(5 ደቂቃ) ijwbv 26—ጭብጥ፦ የመዝሙር 46:10 ትርጉም ምንድን ነው? (th ጥናት 18)

6. እምነታችንን ማብራራት

(4 ደቂቃ) ሠርቶ ማሳያ። g 12/10 22-23—ጭብጥ፦ ስለ ግብረ ሰዶም ምን አመለካከት አለህ? (lmd ምዕራፍ 6 ነጥብ 5)

ክርስቲያናዊ ሕይወት

መዝሙር 131

7. ለትዳር አጋራችሁ ፍቅራችሁን መግለጻችሁን ቀጥሉ

(10 ደቂቃ) ውይይት።

የሠርግ ቀን የደስታ ቀን ነው። (መዝ 45:13-15) ብዙዎቹ ባለትዳሮች በሕይወታቸው ውስጥ በጣም ከሚደሰቱባቸው ቀኖች አንዱ የሠርጋቸው ቀን ነው። ይሁንና ባለትዳሮች በመላው ሕይወታቸው ይህ ደስታ እንዲቀጥል ምን ማድረግ ይችላሉ?—መክ 9:9

ፍቅር መግለጽ ለሰመረ ትዳር በጣም ወሳኝ ነው። ባለትዳሮች የይስሐቅንና የርብቃን ምሳሌ መኮረጃቸው ጠቃሚ ነው። መጽሐፍ ቅዱስ፣ ይስሐቅና ርብቃ በትዳር ዓለም ከ30 ዓመት በላይ ካሳለፉ በኋላም እንኳ ፍቅራቸውን ይገላለጹ እንደነበር ይናገራል። (ዘፍ 26:8) በዛሬው ጊዜ ያሉ ባለትዳሮችስ ፍቅራቸውን እንዲገልጹ ምን ሊረዳቸው ይችላል?

ለሰመረ ትዳር፦ ፍቅር መግለጽ የተባለውን ቪዲዮ አጫውት ከዚያም የሚከተሉትን ጥያቄዎች ጠይቅ፦

  • ባለትዳሮች በስሜት እንዲራራቁ የሚያደርጋቸው ምን ሊሆን ይችላል?

  • ባለትዳሮች የትዳር አጋራቸው በጣም እንደሚወደድ እንዲሰማው ማድረግ የሚችሉት እንዴት ነው?—ሥራ 20:35

8. ለጉባኤው እንደሚያስፈልግ

(5 ደቂቃ)

9. የጉባኤ የመጽሐፍ ቅዱስ ጥናት

የመደምደሚያ ሐሳብ (3 ደቂቃ) | መዝሙር 111 እና ጸሎት