ከግንቦት 27–ሰኔ 2
መዝሙር 42–44
መዝሙር 86 እና ጸሎት | የመግቢያ ሐሳብ (1 ደቂቃ)
1. ከመለኮታዊ ትምህርት የተሟላ ጥቅም አግኙ
(10 ደቂቃ)
ከሌሎች ጋር ሆናችሁ ይሖዋን ለማምለክ የሚያስችሉ አጋጣሚዎችን ተጠቀሙባቸው፤ በተቻለ መጠን በአካል ለመገኘት ጥረት አድርጉ (መዝ 42:4, 5፤ w06 6/1 9 አን. 4)
የአምላክን ቃል ከማጥናታችሁ በፊት ጸልዩ (መዝ 42:8፤ w12 1/15 15 አን. 2)
የመጽሐፍ ቅዱስ እውነት እያንዳንዱን የሕይወታችሁን ክፍል እንዲመራው ፍቀዱ (መዝ 43:3)
መለኮታዊ ትምህርት ፈተናዎችን እንድንቋቋም እንዲሁም ራሳችንን ስንወስን የገባነውን ቃል ጠብቀን እንድንኖር ኃይል ይሰጠናል።—1ጴጥ 5:10፤ w16.09 5 አን. 11-12
2. መንፈሳዊ ዕንቁዎች
(10 ደቂቃ)
-
መዝ 44:19—“ቀበሮዎች በሚኖሩበት ቦታ” የሚለው አገላለጽ ምን ሊያመለክት ይችላል? (it-1 1242)
-
ከዚህ ሳምንት የመጽሐፍ ቅዱስ ንባብ ምን መንፈሳዊ ዕንቁዎች አግኝታችኋል?
3. የመጽሐፍ ቅዱስ ንባብ
(4 ደቂቃ) መዝ 44:1-26 (th ጥናት 11)
4. ውይይት መጀመር
(4 ደቂቃ) ከቤት ወደ ቤት። ግለሰቡ የመጽሐፍ ቅዱስ ጥናት እንዲጀምር ጋብዝ። (lmd ምዕራፍ 5 ነጥብ 5)
5. ተመላልሶ መጠየቅ
(5 ደቂቃ) ከቤት ወደ ቤት። ግለሰቡ በቀጣዩ የሕዝብ ንግግር ላይ እንዲገኝ ጋብዝ። በስብሰባ አዳራሻችን ውስጥ ምን ይከናወናል? የተባለውን ቪዲዮ ተጠቀም። (lmd ምዕራፍ 7 ነጥብ 5)
6. ንግግር
(3 ደቂቃ) lmd ተጨማሪ መረጃ ሀ ነጥብ 4—ጭብጥ፦ ሁሉም ሰው ሙሉ በሙሉ ጤነኛ ይሆናል። (th ጥናት 2)
መዝሙር 21
7. ከሥራ እና ከትምህርት ጋር በተያያዘ ጥበብ የሚንጸባረቅበት ውሳኔ አድርጉ
(15 ደቂቃ) ውይይት።
ወጣቶች፣ የሁለተኛ ደረጃ ትምህርታችሁን ከጨረሳችሁ በኋላ ምን እንደምታደርጉ እያሰባችሁ ነው? በአቅኚነት ለማገልገል የሚረዳችሁ አንድ የሥራ መስክ መርጣችሁ ሊሆን ይችላል። ወይም ደግሞ እንዲህ ያለ ሥራ ለማግኘት የሚረዳችሁ ክህሎት፣ የብቃት ማረጋገጫ ወይም ዲፕሎማ የሚያስገኙ ተጨማሪ ኮርሶችን ለመውሰድ እያሰባችሁ ይሆናል። ወጣትነት አስደሳች ዕድሜ ነው! ያም ቢሆን ውሳኔ ማድረግ ሊያስቸግራችሁ ወይም ሌሎችን የሚያስደስት ውሳኔ እንድታደርጉ ጫና ሊበዛባችሁ ይችላል። ታዲያ ጥበብ የሚንጸባረቅበት ውሳኔ እንድታደርጉ ምን ሊረዳችሁ ይችላል?
ማቴዎስ 6:32, 33ን አንብብ። ከዚያም የሚከተሉትን ጥያቄዎች ጠይቅ፦
-
ከሥራና ከትምህርት ጋር በተያያዘ አስፈላጊ ውሳኔዎችን ከማድረጋችሁ በፊት ግልጽ የሆኑ መንፈሳዊ ግቦችን ማውጣታችሁ ጠቃሚ የሆነው ለምንድን ነው?
-
ወላጆች፣ ልጆቻቸው ማቴዎስ 6:32, 33ን በሥራ ላይ እንዲያውሉ ሊረዷቸው የሚችሉት እንዴት ነው?—መዝ 78:4-7
የተደላደለ ሕይወት ለመምራት ወይም ዝና ለማግኘት ያላችሁ ፍላጎት በውሳኔያችሁ ላይ ተጽዕኖ እንዳያሳድር ተጠንቀቁ። (1ዮሐ 2:15, 17) አንድ ሰው ብዙ ቁሳዊ ሀብት ያለው መሆኑ በራሱ የመንግሥቱን መልእክት መቀበል ከባድ እንዲሆንበት ሊያደርግ እንደሚችል አስታውሱ። (ሉቃስ 18:24-27) ቁሳዊ ሀብትን ማሳደድ ከመንፈሳዊ ሀብትና ስኬት ጋር አብሮ አይሄድም።—ማቴ 6:24፤ ማር 8:36
ዘላለማዊ ባልሆኑ ነገሮች አትታመኑ!—ሀብት የተባለውን ቪዲዮ አጫውት። ከዚያም እንዲህ ብለህ ጠይቅ፦
-
ምሳሌ 23:4, 5 ጥበብ የሚንጸባረቅበት ውሳኔ ለማድረግ የሚረዳችሁ እንዴት ነው?
8. የጉባኤ የመጽሐፍ ቅዱስ ጥናት
(30 ደቂቃ) bt ምዕ. 10 አን. 5-12