ከግንቦት 6-12
መዝሙር 36–37
መዝሙር 87 እና ጸሎት | የመግቢያ ሐሳብ (1 ደቂቃ)
1. “በክፉዎች አትበሳጭ”
(10 ደቂቃ)
ክፉዎች ብዙ ሥቃይና ጭንቀት ያደርሱብናል (መዝ 36:1-4፤ w17.04 10 አን. 4)
“በክፉዎች” ላይ መበሳጨታችንም ሊጎዳን ይችላል (መዝ 37:1, 7, 8፤ w22.06 10 አን. 10)
ይሖዋ በገባው ቃል ላይ መተማመናችን ሰላም ይሰጠናል (መዝ 37:10, 11፤ w03 12/1 13 አን. 20)
ራስህን እንዲህ ብለህ ጠይቅ፦ ‘ክፋትን ለሚያሳዩ የዜና ዘገባዎች ከልክ ያለፈ ትኩረት እሰጣለሁ?’
2. መንፈሳዊ ዕንቁዎች
(10 ደቂቃ)
-
መዝ 36:6—መዝሙራዊው የይሖዋ ጽድቅ “ግርማ እንደተላበሱ ተራሮች” [ወይም “እንደ አምላክ ተራሮች” ግርጌ] እንደሆነ ሲናገር ምን ማለቱ ሊሆን ይችላል? (it-2 445)
-
ከዚህ ሳምንት የመጽሐፍ ቅዱስ ንባብ ምን መንፈሳዊ ዕንቁዎች አግኝታችኋል?
3. የመጽሐፍ ቅዱስ ንባብ
(4 ደቂቃ) መዝ 37:1-26 (th ጥናት 10)
4. ውይይት መጀመር
(3 ደቂቃ) ከቤት ወደ ቤት። (lmd ምዕራፍ 1 ነጥብ 5)
5. ተመላልሶ መጠየቅ
(4 ደቂቃ) መደበኛ ያልሆነ ምሥክርነት። ከዚህ በፊት መጽሐፍ ቅዱስን ለማጥናት ፈቃደኛ ያልነበረን ሰው የመጽሐፍ ቅዱስ ጥናት እንዲጀምር ጋብዝ። (lmd ምዕራፍ 9 ነጥብ 4)
6. ንግግር
(5 ደቂቃ) ijwbv 45—ጭብጥ፦ የመዝሙር 37:4 ትርጉም ምንድን ነው? (th ጥናት 13)
መዝሙር 33
7.‘ለመከራ ጊዜ’ ተዘጋጅታችኋል?
(15 ደቂቃ) ውይይት።
በዓለም ዙሪያ ያሉ ወንድሞችና እህቶች በተፈጥሯዊም ሆነ በሰው ሠራሽ አደጋዎች የተነሳ ብዙ መከራና ሐዘን ይደርስባቸዋል። (መዝ 9:9, 10) እንደ እውነቱ ከሆነ፣ ‘የመከራ ጊዜ’ በየትኛውም ሰዓት ሊከሰት ይችላል፤ በመሆኑም ሁላችንም እንዲህ ላሉት ችግሮች መዘጋጀት ይኖርብናል።
በቁሳዊ ከመዘጋጀት a በተጨማሪ፣ አደጋ ሲከሰት ሁኔታውን ለመቋቋም ምን ሊረዳን ይችላል?
-
አእምሯዊ ዝግጅት አድርጉ፦ አደጋዎች ሊከሰቱ እንደሚችሉ አምናችሁ ተቀበሉ፤ እንዲሁም በዚህ ወቅት ምን ማድረግ እንደምትችሉ አስቀድማችሁ አስቡ። ከቁሳዊ ንብረቶቻችሁ ጋር ከመጠን ያለፈ ቁርኝት እንዳይኖራችሁ ተጠንቀቁ። ይህም አፋጣኝ እርምጃ እንድትወስዱ እንዲሁም ከንብረቶቻችሁ ይልቅ ለደህንነታችሁና ለሕይወታችሁ ቅድሚያ እንድትሰጡ ይረዳችኋል። (ዘፍ 19:16፤ መዝ 36:9) በተጨማሪም አደጋ ከተከሰተ በኋላ ንብረታችሁን ብታጡ ከልክ በላይ እንዳታዝኑ ይረዳችኋል።—መዝ 37:19
-
መንፈሳዊ ዝግጅት አድርጉ፦ ይሖዋ እናንተን ለመንከባከብ ችሎታውም ሆነ ፍላጎቱ እንዳለው እምነት አዳብሩ። (መዝ 37:18) ‘ሕይወታችን ብቻ እንደ ምርኮ ሆኖ’ ቢሰጠን እንኳ ይሖዋ ምንጊዜም አገልጋዮቹን እንደሚመራቸውና እንደሚደግፋቸው አዘውትረን ማስታወስ ይኖርብናል፤ ይህን ማድረግ ያለብን አደጋ ከመድረሱ በፊት ነው።—ኤር 45:5፤ መዝ 37:23, 24
ይሖዋ በገባው ቃል ላይ ጠንካራ እምነት ካለን እሱን ‘በጭንቅ ጊዜ መሸሸጊያችን’ እናደርገዋለን።—መዝ 37:39
አደጋ ቢያጋጥም ዝግጁ ናችሁ? የተባለውን ሺዲዮ አጫውት። ከዚያም የሚከተሉትን ጥያቄዎች ጠይቅ፦
-
በአደጋ ጊዜ ይሖዋ የሚረዳን እንዴት ነው?
-
ለአደጋ ለመዘጋጀት የትኞቹን ተግባራዊ እርምጃዎች መውሰድ እንችላለን?
-
በአደጋ የተጎዱ ሰዎችን መርዳት የምንችለው እንዴት ነው?
8. የጉባኤ የመጽሐፍ ቅዱስ ጥናት
(30 ደቂቃ) bt ምዕ. 9 አን. 8-16
የመደምደሚያ ሐሳብ (3 ደቂቃ) |
a ንቁ! ቁጥር 5 2017 ገጽ 4-6ን ተመልከት።