ክርስቲያናዊ ሕይወት
በJW Library እየተጠቀማችሁ ነው?
JW Library መጽሐፍ ቅዱስን ጨምሮ ሌሎች ጽሑፎችን፣ ቪዲዮዎችንና ኦዲዮ ፕሮግራሞችን ወደ ስልክ፣ ታብሌት ወይም ኮምፒውተር ለማውረድ የሚያስችል ነፃ አፕሊኬሽን (ሶፍትዌር) ነው።
የሚገኘው እንዴት ነው? ኢንተርኔት ላይ የሚገኝ የአፕሊኬሽን ማውረጃ ተጠቅመህ JW Libraryን ጫን። አፕሊኬሽኑን የተለያዩ ዓይነት መሣሪያዎች ላይ መጫን ይቻላል። ኢንተርኔት ላይ ሆነህ አፕሊኬሽኑን ከከፈትክ በኋላ የምትፈልጋቸውን ነገሮች ማውረድ ትችላለህ። ቤትህ ኢንተርኔት ማግኘት ካልቻልክ በመንግሥት አዳራሽ፣ በሕዝብ ቤተ መጻሕፍት ወይም በአቅራቢያህ ባለ አንድ ሻይ ቤት የኢንተርኔት አገልግሎት ማግኘት ትችል ይሆናል። አንድ ጊዜ የምትፈልጋቸውን ነገሮች ካወረድክ በኋላ እነዚያን ነገሮች መልሰህ ለማግኘት ኢንተርኔት አያስፈልግህም። JW Library ላይ በየጊዜው አዳዲስ ነገሮች ስለሚጨመሩ የአፕሊኬሽኑ አዲስ ሥሪት ሲወጣ ለማውረድ፣ የኤሌክትሮኒክ መሣሪያህን አልፎ አልፎ ከኢንተርኔት ጋር ማገናኘት ሊያስፈልግህ ይችላል።
ምን ጥቅም አለው? JW Library የግል ጥናት ለማድረግና በጉባኤ ስብሰባዎች ላይ ለመከታተል በእጅጉ ይረዳል። አፕሊኬሽኑ ለአገልግሎት በተለይም ደግሞ መደበኛ ባልሆነ መንገድ ለመመስከር ጠቃሚ ነው።