በይሖዋ ድንኳን ውስጥ በእንግድነት የሚስተናገደው ማን ነው?
በይሖዋ ድንኳን ውስጥ በእንግድነት መስተናገድ ማለት የአምላክ ወዳጅ መሆን ማለት ነው፤ እንዲህ ዓይነት ሰው በአምላክ ይታመናል እንዲሁም ይታዘዘዋል። መዝሙር 15 የይሖዋ ወዳጅ ለመሆን ምን ዓይነት ባሕርያት ማዳበር እንዳለብን ይገልጻል።
የይሖዋ እንግዳ የሚያደርጋቸው ነገሮች
-
በንጹሕ አቋም መመላለስ
-
በልቡም እንኳ እውነትን መናገር
-
የይሖዋን አገልጋዮች ማክበር
-
ከባድ ቢሆንም እንኳ ቃሉን መጠበቅ
-
በምላሹ ምንም ነገር ሳይጠብቅ የተቸገሩትን መርዳት
የይሖዋ እንግዳ የማያደርጋቸው ነገሮች
-
ሐሜትና ስም ማጥፋት
-
በባልንጀራው ላይ መጥፎ ነገር መሥራት
-
ክርስቲያን ወንድሞቹን መጠቀሚያ ማድረግ
-
ይሖዋን ከማያገለግሉ ወይም ከማይታዘዙ ሰዎች ጋር መወዳጀት
-
ጉቦ መቀበል