ክርስቲያናዊ ሕይወት
JW Libraryን ተጠቀሙበት
ለግል ጥናት፦
-
መጽሐፍ ቅዱስና የዕለት ጥቅስ አንብቡ
-
የዓመት መጽሐፍ፣ መጽሔቶችና ሌሎች ጽሑፎችን አንብቡ። ምልክት ለማድረግ “እልባቱን” ተጠቀሙ
-
ለጉባኤ ስብሰባዎች ተዘጋጁ፤ እንዲሁም መልሶቹን በማቅለም ምልክት አድርጉ
-
ቪዲዮዎችን ተመልከቱ
ለጉባኤ፦
-
ተናጋሪው የሚጠቅሳቸውን ጥቅሶች አውጡ። ቀደም ሲል የተመለከታችሁትን ጥቅስ ለመክፈት “በቅርብ የተነበቡ” የሚለውን ተጠቀሙ
-
በስብሰባዎች ላይ የተለያዩ ጽሑፎችን ይዞ ከመምጣት የኤሌክትሮኒክ መሣሪያችሁን ተጠቅማችሁ የሚወሰዱትን ክፍሎች መከታተልና መዝሙሮችን መዘመር ትችላላችሁ። JW Library በታተመው መዝሙር መጽሐፍ ላይ ገና ያልተካተቱ አዳዲስ መዝሙሮችን ይዟል
ለአገልግሎት፦
-
ፍላጎት ላሳየው ሰው JW Libraryን ተጠቅማችሁ አንድ የሕትመት ውጤት አሳዩት፤ ከዚያም በራሱ መሣሪያ ላይ አፕሊኬሽኑን በመጫን ሌሎች ጽሑፎችን እንዲያወርድ እርዱት
-
“መፈለጊያውን” ተጠቅማችሁ የመጽሐፍ ቅዱስ ጥቅሶችን አውጡ። ጥቅሱን ለማግኘት አንድ ቃል ወይም ሐረግ መጻፍ ትችላላችሁ
-
ቪዲዮ አሳዩ። የቤቱ ባለቤት ልጆች ካሉት የይሖዋ ወዳጅ ሁን ከተባሉት ቪዲዮዎች መካከል አንዱን ማሳየት ትችላላችሁ። አሊያም መጽሐፍ ቅዱስን ለማጥናት እንዲነሳሳ መጽሐፍ ቅዱስን መማር የሚኖርብን ለምንድን ነው? የሚለውን ቪዲዮ ልታሳዩት ትችላላችሁ። ሌላ ቋንቋ የሚናገር ሰው ካገኛችሁ ደግሞ በቋንቋው የተዘጋጀ ቪዲዮ አሳዩት
-
ለምታነጋግሩት ሰው ቀደም ሲል ያወረዳችሁትን በሌላ ቋንቋ የተዘጋጀ የመጽሐፍ ቅዱስ ትርጉም ተጠቅማችሁ አንድ ጥቅስ አሳዩት። እንዲህ ለማድረግ ጥቅሱን ካወጣችሁ በኋላ ቁጥሩን ንኩ፤ በመቀጠልም አቻ ትርጉሞችን ለማየት የሚያስችለውን አማራጭ ንኩ